አውቀው አያጠፉም-ከአጠፉም አላወቁም!

እኔ በራሴ ነፃ ፍላጎትና ምርጫ የመኖር መብት አለኝ። ይህ በነፃነት የመኖር መብት የእናንተን በነፃነት የመኖር መብት እንዳከብር ከተጣለብኝ ግዴታ ጋር እኩል ነው። ስለዚህ፣ ነፃነት የመብትና ግዴታን እኩሌታ ነው። ጌዴታዬን የምወጣው ግዴታህን እስከተወጣህ ድረስ ብቻ ነው። ግዴታቸውን ሳይወጡ “መብታችን ይከበር“ የሚሉ ሰዎች መብታቸውን ነፍጎ ግዴታቸውን እንዲወጡ ካስገደዳቸው ሌላኛው አካል ጋር አንድና ተመሳሳይ ናቸው። ያለበትን ግዴታ በአግባቡ የማይወጣ ማህብረሰብ መብቱን ጠንቅቆ አያውቅም። መብቱን የማያውቅ፣ ግዴታውን አይረዳም፣ ፍትህን አያውቅም፣ ፍትህን አይጠይቅም። በእንዲህ ያለ ማህብረሰበብ የሕግ የበላይነት ሊሰፍን አይችልም። የግለሰብን መብት ሲጥስና ሲደመስስ የሚውል ማህብረሰብ መብት፣ ነፃነት፣ ዴሞክራሲ፣…ወዘተ፣ አይገባውም። “ወያኔ ይጥፋ!“ እያለ የሚፎክርን ወያኔ ቢያጠፋው ወይም ሊያጠፋቸው ሲል ቢያጠፉት፣ አጥፊዎች ተጠፋፉ። በዚህ አይነት በመጠፋፋት ውስጥ በዳይና ተበዳይ፣ መብትና ግዴታ፣ ፍትህና እኩልነት የለም።

የሌሎችን መብት እንዳይጥስ የተጣለበትን ግዴታ እየተወጣ ሌላውም እንደሱ እንዲያደርግ በምሳሌ የሚታገል ነው። እየሱስ ክርስቶስ፣ መሃተመ ገንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ኔልሰን ማንዴላ፣ በዚህ የትግል ስልት ታግለው ያሸነፉና በዚህም ዘላለማዊ ክብር የተጎናፀፉ ናቸው። ነገር ግን፣ አንተ ያልሆንከውን ሌሎች እንዲሆኑ ስትጠይቅ እነሱምን እንደ አንተ እንዲሆኑ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም። በጠቅላላ ጉባኤ በአባላት ነፃና ገለልተኛ ምርጫ የተወከለ አመራር የሌለው የፖለቲካ ፓርቲ ምርጫ 2007 ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን ምን አይነት አስተዋፅዖ ሊያበረክት ይችላል?

ethiothinkthank.com

Advertisements