የሦስት ዘመናት ነፃነት

በአፄው ዘመን “ንጉሱን ከስልጣን ለመፈንቀል አታስብ እንጂ…” ነበር። …ያንን ያሰቡ እነ ግርማሜና መንግስቱ ምን እንደሆኑ ሁሉም ያውቃል።

በደርግ ዘመን “እንኳን ስለ ስልጣን ማሰብ ጭራሽ ሃሳብ ብሎ ነገር እንዳታስብ አለ” የራሱ የሆነ ቁራጭ ሃሳብ የነበረው ሰው ሁሉ ከየቤቱ እየታደነ ተረሸነ። በመንግስትና ህዝብ መካከል የነበረው የመተማመን መንፈስ ላይመለስ ወደመ።

ይህን ሰው በላ ስርዓት አስወግዶ ወደ ስልጣን የመጣው ኢህአዴግ ደግሞ ሌላ የተለየ ነገር ይዞ መጣ። እያየሁና እየሰማሁ “አላዬሁም፣ አልሰማሁም” …በሕይወት እየኖርኹ “የለሁም፣ አልኖርኹም” እንድል ያስገድደኝ ገባ። ያ ካልሆነ እንደ ህፃን ልጅ ቶሎ አኩርፎ በእጁ የገባን ነገር ሁሉ እየወረወረ ወደ እስር ቤትና ስደት ያሳድድ ጀመረ።

ethiothinkthank.com

Advertisements