ሣቂልኝ

ቃል ሳይወጣሽ፣ ምንም ሳትናገሪ
በፈገግታና ሳቅ ብቻ የምታወሪ
እስኪ ውዴ፣ ሁሌም ደ…ስ እንዲለኝ
ፈገግታሽ አይጥፋ፣ ሳቅሽ አይለየኝ

ሣቅሽን ልስማው እንደ ሙዚቃ
ይብቃኝ ቁዘማ፣ ቆፈን ልቤም ይንቃ
ፈገግታሽን እያየሁ ምንም ሳልናገር
በሳቅሽ ጥዑም ዜማ ልደንስ፣ልደንክር
በሃሴት ጮቤ ልርገጥ፣በደስታ ልስከር

ውዴ እባክሽ ሁሌም ሣቂ
ቆፈን ልቤን በደስታ አሙቂ
ሕይወቴን በፍቅርሽ አድምቂ
*****
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements