“ባርነት” የፈረጆቹ ወይስ የግብፃቹ?

“አፄ ሱስንዮስ በነገሰ በ19ኛው ዓመት የፈረንጆች ተወላጅ አቡነ አልፎንዝ መጣ፡፡ ከ 2 ዓመት በኋላም ንጉሱ የፈረንጆቹን ሃይማኖት ስለተቀበለ በኢትዮጵያ ትልቅ ስደት ሆነ፡፡ ይህን  ሃይማኖት ያልተቀበለ በሙሉ… እጣው ስደት ሆነ፡፡
…እኔ በሃገሬ መፅሃፍት ሳስተምር ብዙዎቹ ጓደኞቸ ጠሉኝ፡፡…ከሁሉ ሰው፤ ከፈረንጆቹና ከግብፃዊያን ጋር እስማማለሁ፡፡ መፅሃፍትን ሳስተምርና ስተረጉም ፈረንጆቹ እንዲህ እንዲህ ይላሉ፡፡ ግብፃዊያኖች ደግሞ (ኦርቶዶክሶች) እንዲህ እንዲህ ይላሉ እላለው፡፡ እኛም ብንመረምር ይህን ሁሉ እናውቃለን እላለሁ እንጅ ይህ መልካም ነው ይህ ደግሞ ክፉ ነው አልልም፡፡ ግብፃቹ የፈረንጅ፣ ፈረንጆቹ ደግሞ የግብፃዊያኖቹ እመስላቸዋለው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ጠሉኝ…”

“…ከፀሎት በኋላም ስራ ስለሌለኝ ሁልጊዜ ስለሰዎች ክፋትና ሰዎች በእርሱ ስም ሲበድሉ፣ ወንድሞቻቸውን ጉዋደኖቻቸውን ሲያባርሩ እና ሲገድሉ ዝም በማለቱ ስለፈጣሪ ጥበብ አስብ ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ ፈረንጆቹ አየሉ፡፡ ነገር ግን ያገሩ ሰዎችም ከነሱ የባሰ ክፋት ሰሩ እንጅ ፈረንጆቹ ብቻቸውን አልነበረም የከፉት፡፡ የካቶሊክ ሃይማኖት የተቀበሉት ኦርቶዶክሶች
የመንበረ ጴጥሮስን እውነተኛዋን ሃይማኖት ክደዋልና የእግዚያብሔር ጠላቶች ናቸው አሉ፡፡ ስለዚህም አሳደዱአቸው፡፡ ኦርቶዶክሶችም ለሃይማኖታቸው እንዲሁ አደረጉ፡፡…”
ሐተታ ዘርዓ ያዕቆብ ገፅ 2-3

መልመጃ:
1) በኢትዮጲያ ምድር “ግብፃዊያኖቹ” እና “ፈረንጆቹ” የተጣሉት ለምንድን ነበር?

ethiothinkthank.com

Advertisements