“የሃይል እውቀት” እና “የእውቀት ሃይል” በቀበሌ

ባለፈው ሳምንት፣ በ34 ዓመቴ ለመጀመሪያ ግዜ የቀበሌ ነዋሪነት  መታወቂያ አወጣሁ። “እስከ አሁን ለምን…?” ጥሩ። ለአቅመ-መታወቂያ ከደረስኩበት ግዜ ጀምሮ ለ15 ዓመታት መታወቂያ ያላወጣሁት አንድ ነገር በጣም ስለምጠላ ነው። ሆኖም ግን፣ አልቀረልኝም!

….ቆይ ግን፣ አንተ የ01 ቀበሌ መረጃ ሰራተኛ፤ “እድሜዬ 34፣ የተወለድኩበት ዓመት 1974 ዓ.ም” ስልህ፣ “የተወለድከው በ1973 ዓ.ም ነው!” ብለህ የኖርኩትን እውነት በቁንፅል እይታህ ያሰላህው፥ “እድሜዬን’ኮ የኖርኩት እኔ ነኝ፣ ደግሞም የሂሳብ አስተማሪ ነኝ” ስልህ፣ የንቀት ፈገግታ አሳይተህኝ መታወቂያዬ ላይ “1973 ዓ.ም” ብለህ በመፃፍ የተወለድኩበትን ቀን ከእኔ ከባለቤቱ በላይ ላወቅኽ አላዋቂ፣ መቼም  ከወለደችኝ እናቴ በላይ አታውቅ። እኔ’ስ እናቴ በየአመቱ ታህሳስ 19 ደውላ ልደቴን የምታስታውሰኝ፣ ተማሪዎቼ “መልካም ልደት ቲቸርዬ” ብለው የሚያበስሩኝ መ፡ም፡ህ፡ር ነኝ። አንተ ማን…ምንድን ነህ?

እድሜዬ የኖርኩት፣ ማንነቴም የሆንኩት ነው። የአንተ ማንነት’ኮ በተቀመጥክበት ነው፣ ከወንበሯ ስትነሳ ማንም፣ ምንም ነህ። ያኔ እንኳን የሰው እድሜ ልትወስን፣ የኖርከው ሕይወት ስለሚያሳፍርህ እድሜህን ትቀሽባለህ። እኔ እድሜዬ ቆጥሬ ማስረዳት እችላለሁ፣ አንተ ግን መታወቂያውን “እምቢ አልሰጥም” ማለት ብቻ ነው የምትችለው። አየህ ወንድሜ፤ የኔ ሃይል ከእውቀት የመነጨ ነው፤ የአንተ እውቀት ግን ሃይል ነው። በእንዳንተ አይነት ሰው ክብሬ እንዳይዘለፍ ስል የቀበሌ ፅ/ቤት ደጃፍ ሳልረግጥ ለ15 ዓመታት ያለ መታወቂያ ኖርኹ። በዚህ ግዜ ውስጥ እንኳን ትንሽ ጋት ፈቀቅ አትሉም። አንተ የቀበሌው ሊቀመንበር፣ መታወቂያ የሚሰጠኝ የቀበሌው ነዋሪ በመሆኔ ላይ የተመሰረተ ግዴታ እንጂ በቀበሌ ስብሰባ ላይ ከመገኘት ጋር  የተጣመረ ግዴታ አይደለም።
ኧሁሁሁ…ልቦና ይስጣችሁ!!!!

ለምወድህ *አቡቤ*

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s