‘የእንካ-ግን-አትንካ’ ፖለቲካ!

“ዋ…! አሁን ምርጫ ደርሷል! በዚህ ወቅት እንዲት ነገር ኮሽ እንድትል አይፈለግም!”  ብሎ ምክር ብጤ ማስጠንቀቂያ ለሰጠኝ ወዳጄ… “ይህ ከሆነ ታዲያ ‘በምርጫ ወቅት መምረጥ እንጂ *ማሰብ፣ መናገር፣ መፃፍ ክልክል ነው!*’ የሚል አዋጅ ቢወጣ’ኮ መልካም ነበር” የሚል ሃሳብ አቀረብኩለት። በሃሳቤ ደ…ስ ይሰኛል ብዬ ስጠብቅ በተቃራኒው ባየኝ ቁጥር ለንቦጩን ይጥልብኛል። ታዲያ እሱ እንዲሆን የሚፈልገው እና እኔ ባቀረብኩት ሃሳብ መካከል ያለው ተቃርኖ ምን እንደሆነ ለማሰብ ብሞክር ፍፁም ሊገባኝ አልቻለም። “በነፃነት ማሰብ፣መናገርና መፃፍ ይቻላል!” ወይም ደግሞ “…አይቻልም!” ብሎ እርፍ ነው’ጂ፣ “ይቻላል፣ ግን አይቻልም” እያሉ … እኛን ‘ማኖ’ ማስነካትና ‘ፔናሊቲ’ መስጠት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው?
“በነፃነት ማሰብ፣መናገርና መፃፍ አ…ይ…ቻ…ል…ም!” ብሎ በ…ቃ ግልግል!!!  ‘አላየሁም’ አንድ ናት፣ ‘አይቻለሁ’ ግን ሰባት ናት’ አለ ያገሬ ሰው!
“እዩ ግን እንዳታዩ፣
ስሙ ግን እንዳትናገሩ፣
አንብቡ ግን እንዳትፅፉ…”
እንካ-ግን-አትንካ ፖለቲካ…ኤጭ

ethiothinkthank.com

Advertisements