ጠንጋራ ፍቅር

ማን ነው የሚናገር ደፍሮ፣
የሚኖር እንዳፈቀረው ተፈቅሮ።
ማን ነው ያፈቀረውን ያፈቀረ፣
በፍቅሩ ልክ ፍቅርን የተቸረ?

ኤዲያ…ምንድነው “ፍቅር”?
የሚኖሩበት አፍቃሪና ተፈቃሪ?
በቅናት ሟችና በምቾት ኗሪ?

እንደዚህ ነው’ዴ ፍቅር?
የሚያፈቅርን መገፍተር፣
የማይወድን ማፍቀር።

የማይወደኝን ካፈቀርኩኝ፣
ያፈቀርኩት ካላፈቀረኝ፣
“ፍቅር” ብሎ ነገር ይቅርብኝ።

ኤጭ… ድሮስ “ፍቅር” ብሎ ነገር፣
ያስመሳዮች ግርግር።
ይበል እ…ል…ም ጥ…ን…ቅ…ር!!!

ethiothinkthank.com

Advertisements