#ቅምሻ

…የይፋትና ጥሙጋ አውራጃን ጣርማበር ተራራ ላይ ሆኖ ሲመለከቱት እግዚያአብሔር ዓለምን ሠርቶ ሲያበቃ የተረፈውን ትርክምክም ያጐረበት ዕቃ ቤቱ ይመስላል። ሸለቆው፥ ጉባው፥ ተራራው፥ ገመገሙ፥ ጭጋጉ፥ አቧራው ሕይወትን አፍኗት ተኝታለች። ያቺ በሌላው አገር የምትጣደፈው፥ የምትፍለቀለቀው፥ የምትንቦለቦለው ሕይወት እዚህ እፎይ ብላለች – በርጋታ፥ በዝግታ፥ ታምማለች። በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ… ሰኞ፥ ማክሰኞ፥ ረቡዕ…ልደታ -(ራጉኤል)- አባ ጉባ – በዓታ – ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ -አቡየ ፃድቁ – የሱስ ክርስቶስ – ሥላሴ- አርባዕቱ እንስሳ – ቶማስ ሰማዕት – መስቀለ የሱስ – ቅድስት ሐና – ቅዱስ ሚካኤል – እግዚአብሔር አብ -(ሩፋኤል)- አቡነ አረጋዊ -(ገብረ ክርስቶስ)- ሕፃኑ ቂርቆስ -ኪዳነ ምሕረት -እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት – ኤዎስጣቴዎስ ፃድቅ – ገብርኤል -ህንፀታ – ማሪያም – ሐዋርያት -ጊዎርጊስ -ተክለ ሃይማኖት -መርቆሬዎስ -ዮሴፍ -መድሃኔ ዓለም -አማኑኤል -በዓለ እግዚኦ -ቅዱስ ማርቆስ -ደመራ -መስቀል -ቅዱስ ዮሐንስ -ገና -ጥምቀት -ፋሲካ – ትፈስሳለች – ትምማለች ሕይወት፥  በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ—
*******
ዳኛቸው ወርቁ፥ አደፍርስ፥ ገፅ ፭ -፮

ethiothinkthank.com

Advertisements

One thought on “#ቅምሻ

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡