አ…ይ ተማሪነት!

“ተማሪነት ሕይወት ነው፣
ተስፋና ውበት የሞላው”፣
እያልኩ ደጋግሜ ብነግረው።
አለኝ “ተማሪነት ተራ ሕይወት”፣
የሚያጨናንቅ በፈተና፣ በጥናት።

ታዲያ ያለኝ ዝም ብዬ ሳስተውል፣
“ዓይንህን እይ”ያልኩት ይመስል፣
የሆነውን’ ማድነቅ ተስኖታል።

እንዲህ ከሆነ የት/ት ሕይወት፣ 
ይሆናል የቢሆን-አለም ተረተረት።
የሰው ትርምስ፣ የሰው ጋጋታ።
ባዶ ግርግር፣ ባዶ ሁካታ።

የ…ለ…ም የ…ለ…ም፣
ተማሪነት እንዲህ አይደለም።
ሕይወት ነው የሚኖሩት፣
የወጣትነት ውበት ምልክት።

እንደ ውድ ፍቅረኛ ስጦታ፣
የተሞላ በትዝታ፣
የሚኖ’ር በትውስታ።

አ…ወ…ይ ሀሮማያ!
ከዕውቀት ባህርሽ ያሰጠምሽኝ፣
በአጉል ልማድ ያስለከፍሽኝ።
ለጥፋቴ በውጤት የቀጣሽኝ፣
ለልፋቴ ዕውቀት የሸለምሽኝ፣
“ተማሪነት” ሲባል ት…ዝ አልሽኝ።

የታህሳሱ ብርድ፣
ልብ የሚያቆረፍድ።
የግንቦቱ ወበቅ፣
ኤርታሌን የሚያስንቅ።
ራስ የሚመታ፣
የሽንት’ቤት ሽታ።
የካልሲው ጠረን፣
ጆሮ የሚ’ደፍን፣
የትዃኑ ንክ…ሻ…ማ’፣
ያስመንናል በጭለማ።
አ…ይ ተማሪነት!

ካ’ገር ቤት የመጣች ቀሚስ፣
እንደ ሚኒ ስትለበስ።
ደ’ሞ እሷም ትንሽ ቆይታ፣
ስትቀየር በአረጓዴ ቱታ።
ቱታዋም ልትሆን ቅያሪ፣
ይገዛል የቻይና ሱሪ።

ሲመጣ የነበረው ጐፈሬ፣
ችምችም ያለ እንደ ኑግ ፍሬ።
ግማሹ ፋ…ራ እንዳይባል፣
ሲቆረጥ ‘ባላቶሊ’ ስታይል።
ሌላው አሳድጐ እንደ ሽፍታ፣
በጣቱ ሲቋጥር-ሲፈታ።
ጠፍቶት የቋጠሮው መፍቻያ፣
ይመስላል የቁም መጥረጊያ።
አ…ይ ተማሪነት!

እንደ በረሃ ጊንጥ፣
በፍርሃት የሚንጥ፣
በአጉል ልማድ የሚያቀብጥ።
በቴንሽን ስፔስ-ለስፔስ የሚያሯሯጥ።

በፈተና ተናዶ፣
በፍቅር ረመጥ ነዶ፣
ከልብስ ማጠቢያ ሻዎር ተወስዶ¡
አ…ይ ተማሪነት!

‘እከሌ እንትን፣ እንትና እንዲህ ነው’፣
እያሉ ተቧድነው፣ ተጣልተው።
እንዲያ የጎሪጥ እንዳልተያዩ፣
ሲመርቁ ተላቅሰው በእምባ ሊለያዩ።
አ…ይ ተማሪነት!
*******
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements
This entry was posted in Amazing Story, ስነ-ፅሁፍ, Comedy on by .

About Seyoum Teshome

ነፃነት መብት አይደለም፣ ሰው መሆን ነው፣ የሕይወት ትርጉምና ፋይዳ ነው። የሰዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴ በሙሉ አንፃራዊ ነፃነትን ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ነው። ይህ ጦማር ገፅ የነፃነቴ ማሳያ፣ ሰው የመሆኔ ምልክት ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s