“የሙቀጫ መቃብር” እና ኢትዮጲያዊነት

ከ20 የሚበልጥ ሙቀጫ ከመሬት ውስጥ ተቀብሮ ብታገኝ ምን ትገምታለህ? ምንልባት ቦታው የአምልኮ ስፍራ እንደሆነ መገመት ሊቀል ይችላል። የሙቀጫ መቃብር የኢትዮጲያዊነት ማሳያ ቦታ እንደሆነ መገመት ቢከብድም እውነታው ግን ያ ነው። ያኔ እንዲህ እንደአሁኑ በጭፍን ጥላቻ ሀገር ማቅ በለበሰችበት የታሪክ ዘመን፣ ሙስሊም መሆን ለሞት-ቅጣት በሚዳርግበት ያ ቀውጢ ዘመን፣ የወሎ ክርስቲያን ሙስሊም ወገኖቹን ደብቆ፣ ጌሾና ብቅል የሚወቅጥበትን ሙቀጫ ከቀበረ በኋላ፤ “ጃንሆን ይህ ‘ጥምቀትን’ አሻፈረኝ ያለ ሙስሊም መቃብር ነው” እያለ ወገኖቹን ከሞት የታደገበት የታሪክ መዘክር ነው። የ#ጀማል_ራሕማን መስዕዋትነት አይግረምህ፣ ኢትዮጲያዊነት በእንዲህ ያለ መስዕዋትነት የተገኘ የክብር ጌጥ ነው።
******
ለአቡቤ

ethiothinkthank.com

Advertisements