የኢህአዴግ ቅዠት

ቻይና ለሺህ አመታት ከተኛችበት እንቅልፏ ነቅታ፣ እንዲህ በፈጣን ሁኔታ ኢኮኖሚዋን ማሳደግ የቻለችው ህዝቦቿን ከመንፈስ ባርነት ነፃ ማውጣት በመቻሏ ነው። በዚህም፣ በቻይና ሥራ ሃይማኖት ነው። ኢትዮጲያ ውስጥ ግን የተገላቢጦሽ ሃይማኖት ሥራ ነው። ከወሩ 30 ቀናት ውስጥ በአማካይ 15 ቀናት ሥራ የሚሰራ ገበሬ ባለበት ሀገር ውስጥ ‘ለተፋጠነ የኢኮኖሚ እድገት ምቹ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶች’ አለን ማለት አይቻልም።

ይህ ለዘመናት በሕብረተሰቡ ውስጥ ሰርፆ የቆየ፣ ኢኮኖሚው ባለበት-እንዲረግጥ ምክኒያት የሆነ፣ በሀገሪቱ ዋና አንቀሳቃሽ በሆነው አርሶ-አደር ዘንድ ያለ የግዜ ግብዓትን በአግባቡ ያለመጠቀም ችግር። በዚህ ላይ ያለን አማራጭ፣ ይህን ችግር መፍታት ወይም ደግሞ ከድህነት ጋር የመሰረትነውን ጋብቻ “የሰላም ያድርግልን” ብሎ አርፎ መቀመጥ።  የኢትዮጲያ ገበሬ፤ በመስመር ለመዝራት፤ እርሻን ደጋግሞ አርሶ ማሳውን ለማለስለስ፣ ኮመፖስት ለመጠቀም፣ ተጨማሪ የጓሮ አትክልቶችን ለማምረት፣ አረም ለማረም፣ አዝመራውን በግዜ እና በአግባቡ ለመሰብሰብ፣ …ወዘተ፣ ለሁሉም ሥራዎች በቂ ግዜ የለውም! በመንግስት የሚቀርቡ የተለያዩ የግብርና ፓኬጆችን መጠቀም እና በግብረና ባለሞያዎች የሚሰጡ ምክሮችን መተግበር በራሱ “ግዜ” የሚጠይቁ ናቸው። የኢትዮጲያ ገበሬ ደግሞ ግዜ የለውም። በበዓል ቀን ሥራ የሚሰራ ከሆነ በእድር እና በማህበር ይወገዛል፣ ከማህበራዊ ኑሮ ይገለላል። እና ታዲያ፣ ኢህአዴግ ይሄን የበሰበሰ የእድገትና ሥራ ማነቆ ሳይቀይር እስከ 2025 የሀገሪቱን ግብርና ምርታማነት በ98% አሳድጋለሁ ማለቱ “ቅዠታም!” አያስብለውም?

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s