ጥሩ ያልነው መጥፎ ነገር

ምንግዜም ቢሆን በሕብረተሰቡ ዘንድ ድህነት እና ድንቁርና “መጥፎ”፤ ልማት እና እድገት ደግሞ “ጥሩ” ናቸው። ነገር ግን በረጅም ዘመን ታሪካችን ልማት እና እድገት አላየንም፣ በእጥረት እና እጦት ሰቆቃ የተሞላው አኗኗራችን፣ ኋላ-ቀር የሆነ አሰራራችን፣ ለእራሳችን የምንሰጠው ዝቅተኛ ግምት፣ ስለሕይወት ፋይዳ ለማሰብ ያለን ደካማ ፍላጎት…ወዘተ፣ ሁሉም የድህነታችን እና የድንቁርና ውጤቶች ናቸው። አንዳንዴ፣ ምናልባት “ጥሩ እና መጥፎ ተቀያይረውብን ይሆን’ዴ?” እያልኩ እጠይቃለሁ። ይሄው “ጥሩ” የምንለው ቀርቶ “መጥፎ” ያልነው ነው ሕይወታችንን የሞላው፣ በአኗኗራችን የሚታየው።
      
ድህነትን እንደ ቅርስ ከትውልድ-ትውልድ ስንቀባበል የመጣንበት ምክኒያት ማህብረሰቡ “ጥሩ ነው” በሚል እሳቤ የተቀበለው ማህበራዊ እሴት፣ ለልማት እና እድገት ፈፅሞ ምቹ ባለመሆኑ ይመስለኛል። ማህብረሰቡ “ጥሩ ናቸው” ብሎ የተቀበላቸው፣ ሆኖም ግን፣ ከነባራዊ እውነታ አንፃር ሲታዩ ለሀገሪቱ ልማት እና እድገት እንቅፋት  ሆነው ሕዝቡን በድህነት አረንቋ ለዘመናት የዘፈቁ፣ “በመሰረቱ መ..ጥ..ፎ” የሆኑ ማህበራዊ ልማዶች እና ደንቦች ስለ ሰረፁ አይደለምን?። ስለዚህ፣ ማህብረሰቡ “ጥሩ” ያለውና የተቀበለውን ነገር “መጥፎ” መሆኑን እምኖ ልማዱን እና ደንቡን ከመተግበር እንዲቆጠብ ማድረግ ይጠበቅብናል።
*****
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements