“ነፃነት” ያለ ብቻ ያሸንፋል!

የእነ ዋለልኝ፣ ጥላሁን እና ማርታ ትውልድ ያነሳው የፍትህና እኩልነት ጥያቄ ለነ መለስ ዜናዊ፣ ሌንጮ ለታና ተፈራ ዋልዋ ትውልድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መነሻ ምክንያት፣ አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት ቁልፍ የሆነ ግብዓት ነው። በወቅቱ የነበረው ፊውዳላዊ አገዛዝ ሥርዓት ከነበሩበት ዘርፈ-ብዙ ችግሮች/ክፍተቶች መካከል ለለውጥ አራማጆቹ በተለየ ሁኔታ ጐልቶ የታያቸው በፍትህና እኩልነት እጦት ምክንያት በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ ይደርስ የነበረው በደልና ጭቆና ነበር።

በዚህም ፍትህና እኩልነት የሰፈነበት ሥርዓት በሀገሪቱ ለመዘርጋት የአንድ ዘመን ልጆች የተለያየ የትግል ስልት ተከትለው፣ እራሳቸውን ኢህአፓ፣ ሚኤሶን፣ ህውሃት፣ ኦነግና፣ ደርግ…ወዘተ እያሉ አደራጅተው ታገሉ፣ አታገሉ፣ ተጋደሉ፣ አጋደሉ፣ እርስ-በእርስ ተባሉ። በመጨረሻም፣ ያ ባለ ጐፈሬ ትውልድ በተየያየ ስልት ያደረገው ትግል አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቷል።

ያለፈው ትውልድ ለፖለቲካ ትግሉ እንደ መነሻ የተወሰደው የፍትህና እኩልነት ጥያቄ፣ በተለይ በትግሉ አሸንፎ ለወጣው ህውሃት/ኢህአዴግ ቅድሚያ የተሰጠውና አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት እንደ መነሻ ፅንሰ-ሃሳብ የተደርጋ የምትወሰደው የዋለልኝ (?) በብሔር እኩልነት ላይ ያተኮረች ፅሁፍ፣ ሁለቱም መሰረታዊ የነፃነት-መርህን (Universal Principle of Liberty) ማዕከል ያደረጉ አይደለም። በመሆኑም፣ የለውጥ ሃይሎች ለአንድ የጋራ ፖለቲካዊ አለማ ከመተባበር ይልቅ፣ በወቅቱ እንደተስተዋለው እርስ-በእርስ መጫረስን አስከትሏል። በመጨረሻ አሸንፎ የወጣው የፖለቲካ ሃይል’ም መሰረታዊ የሆነውን ጥያቄ መመለስ ስለሚሳነው ቀጣዩ ትውልድ የዘረጋውን ፖለቲካዊ ሥርዓት ለመቀየር በተለያየ ስልት ትግል ማድረጉን ይቀጥላል። 

ከላይ ለተዘረዘሩት ችግሮች ዋናው መንስዔ የህዝቡን ጥያቄ በከፊል ለመመለስ መሞከርና ይህንንም እንደ መጨረሻ ግብ አድርጐ መውሰድ ነው። ከላይ ለመጥቀስ እንደ ተሞከረው፣ ላለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን በኢትዮጲያ ለተደረገው የፖለቲካ ትግል እንደ መነሻ ተደርገው የተወሰዱት “የፍትህና እኩልነት” (Justice and Equality) ጥያቄዎች ናቸው። እነዚህ እንደ “መሰረታዊ” መብቶች ሲጠቀሱ መስማት የተለመደ ቢሆን፣ “ፍትህና እኩልነት” በራሳቸው ምሉዕ መብቶች አይደሉም። በራሱ ምሉዕ እና መሰረታዊ የሆነው የሰው-ልጅ መብት፣ “መብት” ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊነት (የሰውነት፣ ሰው-የመሆን) መለያ ተፈጥሯዊ ባህሪ የሆነው ነፃነት ነው። ማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ ትግል ነፃነት እና ነፃነትን ብቻ ማዕከል ያደረገ ሲሆን ወጥና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ (ለውጥ)  ማምጣት ያስችላል።
********
(ፍትህና እኩልነት ለምን እንደ ነፃነት በራሳቸው ምሉዕ መብት እንዳልሆኑ በቀጣይ “ነፃነት” በሚሉ 11 ተከታታይ  ፅሁፎች ለማሳየት እሞክራለሁ።)

ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements

One thought on ““ነፃነት” ያለ ብቻ ያሸንፋል!

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s