ነፃነት (Liberty)፥ ክፍል-4

ሰው በማሰብ ስለ አንድ ነገር ያውቃል፣ ነባራዊ እውነታውን ይረዳል። ስለዚህ፣ ለመፍቀድ ማሰብ – ለማሰብ ፍቃደኛ መሆን አለበት፣ ለማወቅ መፍቀድ – ለመፍቀድ ማወቅ አለበት። በዚህ መሰረት፣ ፈቃድ (will) እና መረዳት (understanding) የሰው-ልጅ ልዩ ተፈጥሯዊ ባህሪያት ናቸው።

ሰው፣ አንድን ተግባር በፈቃዱ ለማከናዎን መረዳት፣ ተግባሩን ለመረዳት ደግሞ በቅድሚያ መፍቀድ ካለበት፣ ፈቃድ እና መረዳትን በተናጠል ማየት አይቻልም። የሰውን ፈቃድ ከመረዳት ወይም መረዳትን ከፈቃድ መነጠል እስካልተቻለ ድረስ ሁለቱን በጥምረት ማየት ያስፈልጋል። ይህ የሚሆነው፣ ፈቃድ እና መረዳትን እንደ መነሻ ምክንያት የሁለቱን ድምር ውጤት በማጥናት ይሆናል።  በፈቃድ እና መረዳት ጥምረት የሚፈጠር ወይም የሁለቱ ድምር ውጤት የሆነው ነገር “ነፃነት” (liberty) ነው።

“ነፃነት” ማለት “ያለ ምንም ውጫዊ ኃይል ወይም አስገዳጅ ሁኔታ (necessity) ነፃ ሆኖ ማሰብ ወይም ማድረግ ነው”።’ ስለዚህ፣ ነፃነት የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ፣ ያለ ውጫዊ ኃይል ወይም የሁኔታዎች አስገዳጅነት “አካላዊ እንቅስቃሴ” (motion) ወይም “ሃሳባዊ እንቅስቃሴ” (thinking) ማድረግ መቻል ነው። ስለዚህ ነፃነት ሊኖር የሚችለው የተንቀሳቃሹ አካል በእራሱ-ተነሳሽነት እና ግንዛቤ መሰረት መንቀሳቀስ ሲችል ነው።

ማንኛውም ሰው ቢሆን አንድን ተግባር በእራሱ ፍቃድና ግንዛቤ መሰረት መጀመር ወይም አለመጀመር፣ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቀጠል ወይም ለማቋረጥ የሚያስችል ተፈጥሯዊ ኃይል አለው። አንድ ሰው ነፃነት የሚኖረው በተረዳው መንገድ ለመንቀሳቀስ በእራሱና ለእራሱ መፍቀድ ሲችል ነው። ሆኖም ግን፣ በፈቃዱ መሰረት፣ ማለትም በተረዳው መንገድ ለመንቀሳቀስ ካልቻለ ግን ነፃነት የለውም። ስለዚህ፣ ነፃነት ማለት ተግባራዊ እንቅስቃሴን በተረዳነው መልኩ ለማድረግ መፍቀድ መቻል ነው።
*******
ይቀጥላል…
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s