ነፃነት (Liberty)፥ ክፍል-8

በተግባራዊ እንቅስቃሴያችን ላይ ካለን ነፃነት እና ከተጣሉብን የሞራል ግዴታዎች አንፃር፣ የሰው-ልጅ መብቶችን ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። የመጀመሪያው፣ ሰው-ሆኖ በመወለድ ብቻ የተገኘ (innate right) ሲሆን፣ ሁለተኛው፣ በተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገኝ (acquired right) ነው።

ሕይወትን በነፃ-ፍላጎትና የግል ምርጫ ለመምራት የሚያስፈልገው ነፃነት የሚገኘው ለተግባራዊ እንቅስቃሴያችን ኃላፊነት መውሰድ ስንችል ነው። ነፃነት፣ ያለ ምንም ውጫዊ ኃይል ወሳኝነት በነፃ-ፍላጎት (free will) የመንቀሳቀስ፣ አማራጭ መንገድን የመወሰና፣ በእራስ ምርጫ የማሰብ፣ ማድረግና የመኖር መብት እንደመሆኑ መጠን፣ ከኃላፊነት ተነጥሎ ሊታይ አይችልም። ነፃነት ያለ ኃላፊነት እንደማይሰጥ ሁሉ፣ መብት’ም ያለ ግዴታ ሊሰጥ አይችልም። ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ የተሰጠ መብት በምንም ዓይነት ቅድመ-ሁኔታ ከማይጣስ ግዴታ ጋር አብሮ የተሰጠ ነው።

መብት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከማጣስ ግዴታ ጋር የተጣመረ ስለሆነ ሁለቱን በጣምራነት ማየት ያስፈልጋል። በዚህ መሰረት፣ ማንኛውም ግለሰብ በሰብዓዊነቱ ብቻ የተጎናፀፋቸውን መሰረታዊ መብቶች “ውስጣዊ የእኔና የአንተ” (internal mine and thine) በማለት በጣምራ ማስቀመጥ ይቻላል። “ውስጣዊ-የእኔ” የግለሰቡን የፍላጎት ነፃነት ሲያመለክት፣ “ውስጣዊ-የአንተ” በሚለው ደግሞ የግለሰቡ ነፃ-ፍላጎት እንደ መብት የሚወሰደው የሌሎች ሰዎችን ነፃነት በማይፃረር መልኩ ተግባራዊ እስከተደረገ ድረስ ብቻ መሆኑን ይጠቁማል (Immanuel Kant, Science of Right)።

በተመሳሳይ፣ ከተወለድን በኋላ በምናደርገው ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገኝን መብት “ውጫዊ የእኔና የአንተ” (external mine and thine) በማለት ማስቀመጥ ይቻላል። “ውጫዊ-የእኔ” አንድ ግለሰብ ባደረገው ተግባራዊ እንቅስቃሴው አማካኝነት በነገሮች ላይ ያለውን የይዞታ ባለቤትነት፤ በግል ፈቃድ እና ምርጫ የመጠቀም መብትን ያመለክታል። “ውጫዊ-የአንተ” የሚለው ደግሞ ነገሮችን በፍቃዱ ሲጠቀም ሌሎች ሰዎች ያላቸውን የመጠቀም መብት በማይፃረር መልኩ መሆን እንዳለበት ያሳያል። ስለዚህ፣ የግለሰብን ነፃነት መገደብ አግባብ የሚሆነው የሌሎችን ነፃነት ለመከላከል ሲሆንና ሲሆን ብቻ ነው (Jhon Stuwart Mills, On Liberty)።  *******
ይቀጥላል…
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s