አንተና እሱ

አንተ……
“እንዴት ይሆናል?” የምትል
ሰውን ለመፈረጅ የምቸኩል
አላዋቂ፣ ፍርደ-ገምድል

እሱን ያሳመነው ምክንያት
ላንተም ቢመስልህ ዕውነት
እሱ የነበረበት ግዜና ቦታ
ቢሆን ያንተ ነባራዊ ሁኔታ
በአጣብቂኙ ራስህን ብታገኘው
በምርጫው እንዳደረገ የፈረጅከው
ይገባሃል አማራጭ እንዳልነበረው
ክፋት አቅዶ የሰራው የመሰለህ
በቅን ልቦና እንደነበር ትረዳለህ

እንዲገባህ ያለበት ሁኔታ
መሆን አለብህ በእሱ ቦታ
የእሱ ዕውነት ላንተም እንዲሆን
ብታስቀምጥ በእሱ ቦታ ራስህን
የፈረጅከው፣ ያጣጣልከውን
አንተም ታደርግና ያደረገውን
እሱም እንዳንተ ፍርደ-ገምድል
ይፈርጅሃል፣ ያጣጥልሃል
ያጣጣልከውን፣ የፈረጅከውን
እሱም ባንተ ቦታ ሲሆን
የሚያደርገውን፣ የሚሆነውን።
*****
ስዩም ተ.
(ለሊዮ ቶልስቶይ)

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s