“ነፃነት” ያለ ብቻ ያሸንፋል!

Ethiopian Think Thank Group

የእነ ዋለልኝ፣ ጥላሁን እና ማርታ ትውልድ ያነሳው የፍትህና እኩልነት ጥያቄ ለነ መለስ ዜናዊ፣ ሌንጮ ለታና ተፈራ ዋልዋ ትውልድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መነሻ ምክንያት፣ አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት ቁልፍ የሆነ ግብዓት ነው። በወቅቱ የነበረው ፊውዳላዊ አገዛዝ ሥርዓት ከነበሩበት ዘርፈ-ብዙ ችግሮች/ክፍተቶች መካከል ለለውጥ አራማጆቹ በተለየ ሁኔታ ጐልቶ የታያቸው በፍትህና እኩልነት እጦት ምክንያት በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ ይደርስ የነበረው በደልና ጭቆና ነበር።

በዚህም ፍትህና እኩልነት የሰፈነበት ሥርዓት በሀገሪቱ ለመዘርጋት የአንድ ዘመን ልጆች የተለያየ የትግል ስልት ተከትለው፣ እራሳቸውን ኢህአፓ፣ ሚኤሶን፣ ህውሃት፣ ኦነግና፣ ደርግ…ወዘተ እያሉ አደራጅተው ታገሉ፣ አታገሉ፣ ተጋደሉ፣ አጋደሉ፣ እርስ-በእርስ ተባሉ። በመጨረሻም፣ ያ ባለ ጐፈሬ ትውልድ በተየያየ ስልት ያደረገው ትግል አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቷል።

ያለፈው ትውልድ ለፖለቲካ ትግሉ እንደ መነሻ የተወሰደው የፍትህና እኩልነት ጥያቄ፣ በተለይ በትግሉ አሸንፎ ለወጣው ህውሃት/ኢህአዴግ ቅድሚያ የተሰጠውና አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት እንደ መነሻ ፅንሰ-ሃሳብ የተደርጋ የምትወሰደው የዋለልኝ (?) በብሔር እኩልነት ላይ ያተኮረች ፅሁፍ፣ ሁለቱም መሰረታዊ የነፃነት-መርህን (Universal Principle of Liberty) ማዕከል…

View original post 149 more words

Advertisements