እናውቃለን!

እነዚህ…
እውነትን የማያውቁ
ለጥቅም የሚጨነቁ
አማራጭ በሌለበት
“ምርጫ” አሉት
ነፃነት ተነፍገን
“ነ…ፃ” እያሉን
ያልሆነውን ቢሉን
ምን ሊገርመን፣
ምን ሊደንቀን?

ሰው የደበደበን፣
የተደበደብንም
ያጭበረበረን፣
የተጭበረበርንም
እኛው ነን…እኛው ነን
ከናንተ ምስክር ሳያሻን
የሆነውን እናውቃለን።
ነፃነት እንደናፈቀን
ጭቆና እንደከረፋን
እናውቃለን…እናውቃለን!!
******
ስዩም ተ.

ethiothinkthank.com

Advertisements

One thought on “እናውቃለን!

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡