“ዋሽቼያለሁ!”

አዎ…አውቃለሁ
“ከልቤ እወድሻለሁ!”
እያልኩ ዋሽቼያለሁ
እንዲህ በውሸት እየማልኩ
በሰው ፍቅር እንዳልቀለድኩ
አሁን “እወድሻለሁ” ስል
ዋሾነቴን ይመሰክራል፣
ሃቄን ይመዘብራል።
ግና ውዴ…
“ዋሽቼያለሁ” ብዬ ስልሽ
እየዋሸሁ እንዳይመስልሽ
ይህን ነገር በውሸት ብናገር
“እውነት…እውነት” እልሽ ነበር
ውሸት…ውሸት ሲባል፣ ሃቅ ይወጣል
እንጂ፣…በውሸት ውሸት ይዋሻል?
ውሸታም’ስ “ዋሽቼያለሁ” ይላል?
-******-
ስዩም ተ.
ሰኔ 16/2007 ዓ.ም

ethiothinkthank.com

Advertisements