የእንጭጭ_ፖለቲካ_ስህተቶች 1967-2007

2007፡ #ኢህአዴግ፡- በልማታዊ-ዴሞክራሲ የምርጫ ገተት፣ የአንድ ፓርቲ አገዛዝ አምባገነንነት በሀገራችን የሰፈነበት፤

2007፡ #ኢዴፓናቅንጅት፡- በ97ቱ ቅንጅት መቃብር ላይ የበቀሉ አረሞች ይህን የአንድ ፓርቲ አገዛዝ አምባገነንነት የደገፉበት፤

#የእንጭጭ_ፖለቲካ_ስህተቶች 1997

1997፡ #ኢህአዴግ፡- በኢንተርሃውሜና ነፍጠኛ ሳውንድ-ትራክ የታጀበ “ብሔር” የሚለውን የገጠር ዜማ ሲዘፍን፣ ከሁሉም ተላምዶ፣ ተዛምዶ፣ ተዋልዶ… “የብሔር ቀውስ” ውስጥ ባለው የከተማ ማህብረሰብ ሃ…ይ…ለ…ኛ ጥፊ የቀመሰበት  (“ያውም ጆሮ የሚያደነቁር፣ አይን የሚያሸዋርር፣ ምርጫ እንዲያጭበረብር ያደረገ ሃይለኛ ጥፊ ነዋ!” አትሉኝም?)

1997፡ #ቅንጅት፡- ፓርላማ ገብቶ መብቱን እንዲያስከብርለት የመረጠውን ህዝብ በጥቂት አዲሳቤዎች የተካበትና “ፓርላማ አልገባም” ብሎ በሀገሪቱ የፖለቲካ መንፈስ ላይ ውሃ የቸለሰበት፤

#የእንጭጭ_ፖለቲካ_ስህተቶች 1987

1987፡ #ሻዕቢያ፡- ፓስታ መብላት፣ ከረንቡላ መጨወት እና ባንዳነት እንደ ዋና የልዩነት መገለጫ ማህበራዊ እሴቶች በመውሰድና በዚህ ላይ የተመሰረተ ብሔራዊ ማንነት ለመገባት እንዲቻል የግብሩ-ይዉጣ ህዝበ-ውሳኔ የተደረገበት፣      

#የእንጭጭ_ፖለቲካ_ስህተቶች 1967

1967፡ #ሕውሃት፡- በማኒፌስቶው ውስጥ “የትግራይ ሪፐብሊክ” የምትለዋን ሀረግ በመጨመር ጠባብ ብሔርተኝነቱን ይፋ ያወጣበት፤

1967፡ #ኢህአፓ፡- “ተኩሶ መግደል ብቻ” ከሚያውቀው የደርግ ጁንታ ጋር መሸሸጊያ እንኳን በሌለበት ከተማ ውስጥ ጦርነት ገጥሞ ወጣቱን ያስፈጀበት…

ethiothinkthank.com