አለ-የለም = አለ

የሌለን ነገር “አለ” ሲሉ
‘አለ’ ያሉትን “የለም” ይላሉ
ይበሉ እንጂ ሁለቱም አሉ
እሱ ቢኖርም፣ ባይኖርም…
“አለ” ማለት አይቀርም
“የለም” የሚል አጠፋም
አስቦ…አስቦ ሳይደርስበት
“አለ” ብሎ ያመነበት
ቢያስበው…ቢያስበው
ሳይደርስበት…ሳያየው
“ፍፁም የለም!” የሚለው
“እርግጥ አለ!” ከሚለው
ምን ለየው?
1+ 0 = 1
1 – 0 = 1
ሁለት ሆነው ለአንድ
ኤጭ ቢኖርም፣ ባይኖርም
እኔን አያስጨንቀኝም!!!
********
ስዩም ተ.
ነሃሴ 2007 ዓ.ም
#atheism #God

ethiothinkthank.com

Advertisements