ቀን-አልባ ቀን

“ርሃብ ስንት ቀን ይፈጃል?”
የደላው ሙቅ ያኝካል
የማይቆጠር ይቆጥራል
አይን ፈጦ
አጥንት ገጦ
የሆድ ጥርስ
ራሱን ግጦ
ጨጓራን ልጦ…
ከንፈር ደርቆ
አንጀት ተጣብቆ
ወዝ ተጨምቆ
አካል አልቆ…
ለሆድ ማስታገሻ
አፍ-ማበሻ
ቁራሽ ጉርሻ
የሌለው ሰው
ምን ቀን አለው?
ምን ቀርቶት
ምንስ ኖሮት
ቀን ይቆጥራል?
ችጋር አጥልቶበት
ሞት አግጦበት
የራበው ሰው
ቀን’ም የለው
የሚቆጥረው!
****
ስዩም ተ.
ነሃሴ 2007 ዓ.ም
#Hunger #Ethiopia_famine #Drought

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s