ዘረኝነት = ድንቁርና – ብሔር

የእራስን ብሔር ወዶ
ሌላው ለሆነው ተናዶ
በራስ ብሔር ተኩራርቶ
ለሌላ ውድቀት ተመኝቶ
አርግዞ ሐዘንና መርዶ
ተሸክሞ የጥላቻ ነዶ
እኔ “እንዲህ ነኝ” ሲል
ብሔርን በጥረት በትግል
በእቅድ ያገኘው ይመስል
እሱ የሆነውን የሆነው በአጋጣሚ 
ደሞ’ስ አለ’ዴ የብሔር አስቀያሚ?

በግል ለሰሩት ጥፋት
የጋራ ማላከኪያ ጥጋት
ከከሰረ ሕይወት ፍጥጫ
መሸሸጊያ፣ ነው ማምለጫ
እንጂ’ማ፣ እንደው ለስም
“ብሔር… ብሔር” ቢባልም
ስም’ጂ አድራሻ የለውም
በስሙ ጥላቻ ቢሰበክም
አይከሰስም፣ አይጠየቅም
ጭፍን ጥላቻ፣ ዘረኝነት
ነው’ጂ የድንቁርና ውጤት
ከብሔር ጋር ምን አገናኝቶት?
*****
ስዩም ተ.
ነሃሴ 2007 ዓ.ም

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s