#የፀረ_ሽብር_ሽብር

እኔ እዚህ ፌስቡክ ላይም ሆነ በ http://www.ethiothinkthank.com የጦማር ገፅ፤ የተለያዩ ሃሳቦች አንፀባርቃለሁ፣ ስለፈለኩት ጉዳይ በነፃነት እፅፋለሁ። ነገር ግን፣ አንባቢዎቼን የሌላ ግለሰብ ወይም ማህብረሰብ መብትን እንዲጣሱ የሚያነሳሱ ወይም የሞራል ድጋፍ የሚሰጡ ፅሁፎችን እንዳላወጣ የሞራል ግዴታ አለብኝ። ከምንም በላይ ግን ሰው በምክንያታዊ አስተሳሰብ እና ግንዛቤ የሚመራ ፍጡር እስከሆነ ድረስ፣ ሃሳቤን የመቀበል እና ያለመቀበል ነፃነቱን በምንም መልኩ ልቀማው አልችልም። በመሆኑም፣ የእኔ የግል አስተሳሰብ እና ግንዛቤን በይፋ ማንፀባረቅ ለሌሎች መብት መጣስ ምክንያት ሊሆን አይችልም። ነገር ግን፣ የነፃነት ጥያቄ ያነሱትን ሁሉ ያለ አግባብ ለማሰር እየዋለ ያለው የሀገራችን የፀረ-ሽብር ሕግ፣ የሰው-ልጅን በምክንያታዊ አስተሳሰብ የማይመራ ግዑዝ ፍጥረት ካደረገ እሳቤ የመነጨ፣ የጭፍን አምባገነንነት መገለጫ ከመሆኑም በላይ፤ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጡትን በነፃነት የማሰብና ሃሳብን የመግለፅ መብቶችን ሙሉ-በሙሉ የደመሰሰ ኢ-ሰብዓዊ የሆነ የሕግ አንቀፅ ነው።
#anti_terrorism, #Zone9_bloggers, #freedom_of_press, #Ethiopia

ethiothinkthank.com