ከራስ_ጥል … ከራስ_ትግል

አብዛኞቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት “ኪራይ ሰብሳቢነትን አጥብቀን እንታገላለን!”  ሲሉ በጣም ያስቁኛል። ኪራይ ሰብሳቢነት ማለት ባለን ንብረት ላይ ምንም አይነት ዕሴት ሳይጨምሩ ተጨማሪ ሃብት ለማፍራት የሚደረግ ጥረት ነው። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የኢህአዴግ ባለስልጣን ለመሆን የቀድሞውን ሥርዓት ማውገዝና የኢህአዴግን የብሔር ፖለቲካ አጥብቆ ማወደስ ነው። ወደ ላይኛው የሥልጣን እርከን ለመውጣትም የሚያስፈልገው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቀድሞውን ሥርዓት ማውገዝ እና ያሁኑን ማወደስ ነው።

የኢህአዴግ የብሔር ፖለቲካ፣ ከብቃት ይልቅ በፖለቲካ ታማኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተ፣ ምንም ዓይነት የአቀራረብ፣ የአመለካከት ወይም የአቋም ለውጥና መሻሻል ባለማድረግ ተጨማሪ ስልጣን፣ ሃብትና ጥቅም የሚገኝበት ሥርዓት እንዲሆን አድርጐታል። በመሆኑም፣ ሥርዓቱ በራሱ ኪራይ ሰብሳቢነት ነው፣ የሥርዓቱ አመራሮችም በአብዛኛው ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው። ስለዚህ “ኪራይ ሰብሳቢነት እንታገላለን!” ሲሉ “ከራሳችን ጋር እንታገላለን” ከማለት ያለፈ ትርጉም የለውም።

ከራስ-ጥል ከሌለ ከራስ-ትግል አይኖርም፣ ሊኖርም አይችልም። ኢህአዴግ ደግሞ፣ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ የማያድግ፣ ከግዜ ጋር የማይበስል፣ ሁሌም ልክ እንደ 20 ዓመት ግልፍተኛ ጐረምሳ፣ ፍፁም ትዕግስት አልባና እልኸኛ ነው። ፓርቲው ከአባላቱም ሆነ ከአንዳንድ የማህብረሰብ ክፍሎች ዘንድ ለሚነሱ የለውጥና መሻሻል ሃሳቦችን በአግባቡ ለማስተናገድ ትዕግስት የለውም። በዚህ ሁኔታ ኢህአዴግ መቼም ቢሆን ከራሱ-አይጣላም፣ ከራሱ-አይታገልም። መቼም ቢሆን ኢህአዴግ ኪራይ-ስብሳቢነትን አይታገልም። ከራሱ ታግሎ አያሸነፍም፣ አያሸንፍም!!!
#EPRDF, #TPLF, #ANDM, #OPDO, #SPDM #Rent_seeking_ethiopia

ethiothinkthank.com