ቀማሽ_መንግስት

ሙዚቃ በጥዑም ዜማና ቅኝት ማህበራዊ ዕሴቶች የሚዳሰሱበት፣ …የሙዚቀኛው የግል ብቃት የሚንፀባረቀወበት ጥበባዊ ስልት ነው!
“ሙዚቃ ሕይወቴ፣ ግዕዝና እዝል
አራራይ አራራይ የተሰጠሽ ከላይ“

ሙዚቃ ከነፍስ ጥሪ ጋር በመንፈስ መቆራኘት ነው። በአዋጅና በመመሪያ የሚፈቀድና የሚከለከል ቁስ-አካል አይደለም።
“ያሬዳዊ ስልት፣ የሰማይ ፀጋ
አራራይ አራራይ የተሰጠሽ ከላይ“
አቆራኘሁት ነፍሴን ካንቺ’ጋ“

እንዲህ ያለ ጥበባዊ ሙዚቃ ሽልማቱ መንፈሳዊ እርካታ ነው። ቴዲ አፍሮ የኢህአዴግን የብሔር ዜማ እንዲህ አድርጎ አዚሞታል። ይህ ቴዲ አፍሮን በግሉ የላቀ የሞራል ስብዕና፣ በሕዝብ ዘንድ የማይነጥፍ ዝና እና አክብሮት እንዲያገኝ አስችሎታል።
“ባገሬ ቅኝት፣ የብሔር ቋንቋ
እደሰታለሁ እኔ አላዝንም በቃ
በአፋር ሲዳማ፣ በጋምቤላ ቶም
ለ’ቂት ዳንኪራ፣ እኔ አላዝንም ከቶም…”

ግን..ግን…መንግስት ጥበብ የለውም፣ መንግስታዊ ጥበብ፣ መንግስታዊ ሙዚቃ የለም። ሙዚቃ የጥበብ ነው። ጥበብ የግለሰብ ነው››› ጥበብ የማህብረሰብ ነው። ጥበብ የእኛ ነው። የዚህ ሀገር መንግስት ጨውና ዘይቱን በእጁ ይዞ የምግቡ ጣዕም በእሱ ፍቃድ የተገኘ እንደሆነ፣ ፀሃፊና ጋዜጠኛ አስሮ የማነበው መፅሃፍና ጋዜጣን ይዘት ይወስናል….ብሎ ብሎ አሁን ደግሞ ለጆሮዬ ጥዑም የሆነውን ሙዚቃ ይመርጥልኝ ገባ። እሺ አሁንስ ፀሃዩ መንግስታችን….አሁን መቀረህ? እኳን ኑሮዬን ስሜቴን መቆጣጠር ከሚሻ መንግስት ጋር ምን ዓይነት ነፃነት…ምን ዓይነት ሕይወት አለ? እግዚዖ ማህረነ….  
#Teddy_Afro_Concert_On_Facebook

ethiothinkthank.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s