እንዴት እውነት ለዕውቀት ይገዛል?

#እውነት፦ በነባራዊ እውነታ ውስጥ ያሉ ግዑዝና ህያው ፍጥረታት እና ተፈጥሯዊ ክስተቶች ናቸው። በአጠቃላይ፣ ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ እውነት ስለሌለ፣ እውነት ማለት #ተፈጥሮ ናት።

#ዕውቀት፦ በነባራዊ እውነታ ውስጥ ስላሉት ፍጥረታት እና ክስተቶች፣ በአጠቃላይ ስለ ተፈጥሮ ያለን #ምክንያታዊ_ግንዛቤ ነው።

#ከፍጥረታት ሁሉ በተለየ የላቀ ምክንያታዊ ግንዛቤ ያለው ፍጡር ሰው ነው።

ስለዚህ፣ #በእውነት_እና_ዕውቀት መካከል ያለውን ንፅፅር #ከተፈጥሮ_እና_ሰው አንፃር መግለፅ ይቻላል።  

#የሰው_ልጅ ሦስት #ተፈጥሯዊ ገደቦች አሉበት፦ የቦታና የግዜ ገደቦች።

#የቦታ_ገደብ፦ ሰው በአንድ ግዜ በሁሉም ቦታ መገኘት አይችልም።
#የግዜ_ገደብ፦ ሰው በአንድ ቦታ ለዘላለም መገኘት አይችልም።

#ሕይወት ማለት በሁለቱ ተፈጥሯዊ ገደቦች ውስጥ ሆኖ #በራስ_ተነሳሺነት የሚደረግ #ተግባራዊ_እንቅስቃሴ ነው።

#በራስ_ተነሳሺነት የሚደረጉ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ለሁለት ይከፈላሉ፦ አካላዊዊ_እና_ሃሳባዊ።

#አካላዊ_እንቅስቃሴ፦ በቦታ፣ ግዜና በአካላዊ አፈጣጠር የተገደበ ተግባራዊ እንቅስቃሴ።

#ሃሳባዊ_እንቅስቃሴ፦ከቦታ፣ ግዜና አካላዊ አፈጣጠር ገደበ ውጪ የሆነ ተግባራዊ እንቅስቃሴ።

#ፍጥረታት የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በሦስት ደረጃዎች ይከፈላሉ።

#ግዑዝ፦ ፍፁም በሆነ የቦታና ግዜ ገደብ ውስጥ ስለሆኑ በራሳቸው_ተነሳሺነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉ ፍጥረታት ።

#ተክል፦ የፍፁም የሆነ የቦታ ገደብ ያለበት፣ ነገር ግን አካላዊ ቅርፅና_ይዘት ለውጥ በማድረግ በራሱ_ተነሳሺነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ፍጡር፣

#እንስሳ፦ በራሱ_ተነሳሺነት ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ፍጡር።

#ሰው_እንስሳዊ፦ በራሱ_ተነሳሺነት ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ #አካላዊ_እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ፍጡር።

#ሰው_ምክንያታዊ፦ በራሱ_ተነሳሺነት
ሃሳባዊ_እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ፍጡር።

#ምክንያታዊ_ግንዛቤ፦ ሰው ከቦታ፣ ግዜና፣ የአካላዊ አፈጣጠር ገደብ ውጪ ሆኖ በሚያደርገው ሃሳባዊ እንቅስቃሴ።

#ዕውቀት፦ በሃሳባዊ እንቅስቃሴ የሚገኝ #ምክንያታዊ_ግንዛቤ።

በመሆኑም፣ #እውነት_ለዕውቀት_ይገዛል!!

http://ethiothinkthank.com

ethiothinkthank.com

Advertisements