#ለውጥ_በዕውቀት_እንጂ_በጥይት_አይመጣም!!

ኢትዮጲያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ሆነ የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ የፖለቲካ ሃይሎች ተመሣሣይ ‘አላማ’ ነው ያላቸው። የሁሉም የትግላቸው አላማ በስልጣን ላይ ያለውን #መንግስት_ማስወገድ ነው። ይሄ #መፈንቅለ_መንግስት እንጂ የሥርዓት ለውጥ አይደለም።

በዚህ ዘመን፣ በተወሰነ የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ መሰረት ሳይኖረው፣ በግለሰቦች (በባለስልጣናት) ላይ ብቻ የተንጠለጠለ   #መንግስታዊ_ሥርዓት (Oligarchy) ሊኖር የሚችልበት አጋጣሚ የለም። ለምሳሌ፣ አንዳንዶች “የኢህአዴግ መንግስት ህዝባዊ መሰረት የለውም!” የሚል የተሳሳተ እሳቤ አላቸው። ነገር ግን፣ እንኳን ኢህአዴግ ደርግ ራሱ ያለ ምንም ህዝባዊ ድጋፍ 17 ዓመት በስልጣን ላይ ባልቆየ ነበር (በተለይ የተሜን #የመሬት_ለአራሹ ጥያቄን ጠልፎ_በኪሴ በማድረጉ…)።

#ዘላቂ_ለውጥ ሊመጣ የሚችለው #የመንግስት_ለውጥን ሳይሆን #የህዝብ_ለውጥን አላማ ባደረጉ የፖለቲካ ሃይሎች ብቻ ነው። በመሆኑም፣ የመንግስት ለውጥ እንደ “ግብ” ሊያዝ ቢችልም አንድ የፖለቲካ ድርጅት የተመሰረተበት፣ የሚታገልለት “አላማ”  ሊሆን ግን አይችልም። ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ፣ በፖለቲካ ትግል የሚመጣ ለውጥ ብቻ ሳይሆን በአቋራጭ ፥ በመፈንቅለ-መንግስት የሚመጣ ለውጥ እንኳን #ህዝባዊ_መሰረት ከሌለው ዘላቂ ሊሆን አይችልም።

ህዝባዊ መሰረት ያለው ለውጥ በዋናነት የአብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል #የፖለቲካ_ንቃተ_ህሊና በማጐልበትና በህዝቡ ዘንድ ያለውን የለውጥ ፍላጐት በማሳደግ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ነው። ፅንሰ-ሃሳቡን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ባለፈው ግማሽ ክ.ዘመን በሀገራችን የተደረጉትን የለውጥ ሂደቶችን በንፅፅር መመልከት በቂ ነው።

አንደኛ፦ በ1950ቹ አጋማሽ ላይ የእነ ግርማሜ እና መንግስቱ ነዋይ የመፈንቅለ-መንግስት ሙከራ፣ እና በ1960ቹ አጋማሽ ላይ የተደረገው የተሳካ መፈንቅለ-መንግስት። ሁለተኛ፦ ህወሃት ከ1967-77 ዓ.ም ድረስ ለ10 ዓመታት ያደረገው ያልተሳካ የትጥቅ ትግል፣ እና ትግሉን #ህዝባዊ_መሰረት እንዲኖረው በማድረግ ከ1977-83 ዓ.ም ድረስ የተደረገው የትጥቅ ትግል። 

በአጠቃላይ፣ በታንክና መትረየስ ተደግፎ የቆመ ሥርዓት #በዕውቀት_እንጂ_በጥይት አይለወጥም። አሁን በሀገራችን ያሉት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ግን #ታንክን በወንጭፍ ለመጣል የሚታትሩ አጉል ጀብደኞች ናቸው። ባለ ታንኩ’ም ድንጋይ ወደ ተወረወረበት ሁሉ መተኮሱን አላቆመም።

ethiothinkthank.com

Advertisements