ለብሔራዊ_የዕቅድ_ኤጀንሲ

1ኛ፦ የኢንዱስትሪ ዘርፍ #መሪ_ሚና የሚጫወትበት ኢኮኖሚ መፍጠር የሀገሪቱ ራዕይ ነው። 

2ኛ፦ በኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው #ለማኑፋክቸሪግ ንዕስ_ዘርፍ ነው።

3ኛ፦ ለማኑፋክቸሪግ ዘርፍ መሰረት ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቁት የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት (ጥ.አ.ተ) ናቸው።

4ኛ፦ በGTP-I ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት መጠን የጥ.አ.ተ ድርሻ ከ1.3% ወደ 1.2% ቀንሷል።

5ኛ፦ ከአንድ ዓመት በፊት፣ ለጥ.አ.ተ እድገት ማነቆ የሆነው ቁልፍ ችግር #የሥራ_አመራር_ክህሎት ማነስ እንደሆነ በጥናት ላይ ተመስርቼ ለማስረዳት ሞክሬ ነበር።

6ኛ፦ ለጥ.አ.ተ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ለችግሩ መፍትሄ ይሰጣሉ የተባሉት የTVET ተቋማት ናቸው።

7ኛ፦ #የTVET_ተቋማት በሥራ_አመራር እና ተያያዥ የቢዝነስ ት/ት መስኮች ስልጠና መስጠት ካቆሙ 5 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል።

8ኛ፦ ስለዚህ፣ የTVET_ተቋማት በማያሰለጥኑበት የስልጠና ዘርፍ የጥ.አ.ተን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የሥራ_አመራር ሞያና ሞያተኛ (Expertise & Experts) የላቸውም።

9ኛ፦ በመሆኑም፣ በGTP-II ለጥ.አ.ተ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና የመስጠቱ ሃላፊነት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ በዋናነት ለዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት አለበት።

10ኛ፦ ከ1 ዓመት በፊት ለሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ጉዳዩ ለማሳወቅ በግሌ ጥረት አድርጌ የነበረ ቢሆንም የተሰጠኝ ምላሽ ግን #የቀን_ጅብ የሚል ስድብና ማስጠንቀቂያ ነበር።

11፦ የጥ.አ.ተ ዘርፉን ችግር መቅረፍ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የተሳነው የፌደራል TVET ኤጀንሲ GTP-I አፈፃፀሙ ተገምግሞ በጥ.አ.ተ ዘርፍ ልማት እና #በኢንዱስትሪ_ኤክስቴንሽን ስም የሚመደብለት በጀት በGTP-II ወደ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ፈሰስ መደረግ አለበት። 

ethiothinkthank.com

Advertisements