የደሃ እንቅልፍ…

ሀብታም ቢተኛ ደልቶት
ጉዳዩ ሞልቶ፣ ተሳክቶለት
እሱ ቢተኛ ምን አለበት
ለነገሩ ቢተኛ-ባይተኛ
ቸነፈር እና ረሃብተኛ
የለበትም እንደ እኛ
ይመቸው!…ይተኛ!

ህዝቤ በችጋር ሊሞት
የሞት-ጥላ አጥልቶበት
አይን ፈጦ…አጥንት ገጦ
ከንፈር ደርቆ…አንጀት ተጣብቆ
ወዝ ተጨምቆ…አካል አልቆ
ለሆድ ማስታገሻ…አፍ-ማበሻ
ቁራሽ ጉርሻ ከሌለው ሰው
የአደራ ቃል ተቀብለው
የሚተኙ ለ…ጥ ብለው
እውን እኚህ ሰው ናቸው?
ወይስ ናቸው ባዶ ገለባ
ግዑዝ ነገር ስሜት አልባ
የሰው ችግር፣ የሰው እምባ
ከሃሳባቸው ዘልቆ የማይገባ
****
ስዩም ተ.
መስከረም 2008 ዓ.ም
****

ethiothinkthank.com

Advertisements