“ለኪራይ ሰብሳቢ ህዝብ፣ ሙሰኛ መንግስት አዘዘለት” እ…ሰ…ይ!

ኪራይ ሰብሳቢነት አንድ ግለሰብ የማይገባን ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። የማይገባ ጥቅም ለማግኘት እንቅስቃሴ እያደረገ ያለ ግለሰብ (ቡድን) ጥረቱ እንዲሳካ ሌላ የማይገባ ጥቅም ፈላጊ አካል ያስፈልገዋል። ሙስና በእነዚህ አካላት መካከል የሚደረግ ተገቢ ያልሆነ የጥቅም ልውውጥ ነው።

ለምሳሌ፣ በትክክለኛው የሊዝ ዋጋ መሬት በመግዛት የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት የሚፈልግ ባለሃብት ለአከባቢው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ ይከፍለዋል። በወሬውና በወሬ አቀባይነቱ ብቻ ከአንድ የገጠር ወረዳ መጥቶ ሃላፊነት የተሰጠው ካድሬ ደግሞ “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” በሚል የኪራይ ሰብሳቢነት እሳቤ ታንፆ ያደገ እንደመሆኑ፣ ያለ ምንም ጥረት የመጣለትን ጥቅም “እምቢ” አይልም።

እርግጥ ነው፣ መንግስት ቅጥ-ያጣ ሙስና ውስጥ ተዘፍቋል፣ የተዘፈቀበት ባህር ግን ሕዝቡ ራሱ ነው። በተለይ የከተማው ማህብረሰብ ከሞላ-ጎደል ሁሉም በኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ የናወዘ ነው። ስለዚህ፣ ሙስና ከኪራይ ሰብሳቢነት ባህር ውስጥ የተቀዳ ትንሽ ውሃ ነው። “ሌባን ሌባ ቢሰርቀው ምን ይድንቀው” ነው ነገሩ…

ethiothinkthank.com

Advertisements

One thought on ““ለኪራይ ሰብሳቢ ህዝብ፣ ሙሰኛ መንግስት አዘዘለት” እ…ሰ…ይ!

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡