“ዝ…ም” አልን!

ስንናገር…”ፀረ-ሰላም…
…ጭር ሲል አይወዱም”
ስንናገር…”ፀረ-ልማት…
…የዴሞክራሲ ጠላት”
ስንናገር…”ነውጠኛ…
…ድሮ-ናፋቂ ነፍጠኛ
…ጠባብ ብሔርተኛ”
ስንናገር…”አክራሪ…
…ፀረ-ህዝብ አሸባሪ”
ስንናገር…”ተንበርካኪ…
…የሻቢዕያ ተላላኪ….”

ስንናገር……ስንናገር
ሲሰድቡን እንዳልነበር
ዛሬ ላይ “ዝም” አልን
በቃላት የሰደቡንን፣
በተግባር ሆነው እያየን
ዝምም፣ ጭ…ጭ አልን
ለውጥ አይቀርም ብለን…
****
ህዳር 29/2008 ዓ.ም

ethiothinkthank.com

Advertisements