አመፅና ተቃውሞ በራሱ ልማትና ዴሞክራሲ ነው

ባሳለፍነው የ2008 ዓ፣ም የታየው ህዝባዊ ተቃውሞና አመፅ በአመቱ የመጨረሻ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል። በአዲሱ አመትም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ግጭትና አለመረጋጋት እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን፣ በ2008 ሐምሌና ነሃሴ ላይ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የነበረው አይነት እንቅስቃሴ አሁንም አለ ለማለት አያስደፍርም።  ይህን በማስመልከት አንዳንድ የገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ሀገሪቷን ሊበታትናት ተቃርቦ የነበረው የፖለቲካ … Continue reading አመፅና ተቃውሞ በራሱ ልማትና ዴሞክራሲ ነው

መሪዎቻችን ስልጣን ላይ ሙጭጭ የሚሉባቸው ሦስት ምክንያቶች

የእኛ ሀገር ባለስልጣናት ከስልጣን መውረድ በጣም ያስፈራቸዋል። ይህ ከሚኒስትር እስከ ቀበሌ ሊቀመንበር ባሉት የስልጣን እርከኖች የሚስተዋል ችግር ነው። በራስ ፍቃድ ስልጣን መልቀቅ ቀርቶ፣ “በስራው ላይ ከፍተኛ የአቅም ማነስ ችግር አለበት” የተባለ ባለስልጣን እንኳን ከስልጣኑ ወርዶ-አይወርድም።  አንዳንድ ምሳሌዎችን ለመጥቀስ ያህል፤ ከሚኒስትርነት ወረደ የተባለ ባለስልጣን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ይሆናል፣ ከክልል ወይም ከዩኒቨርሲቲ ፕረዘዳንትነት የወረደ ቀጣይ … Continue reading መሪዎቻችን ስልጣን ላይ ሙጭጭ የሚሉባቸው ሦስት ምክንያቶች

ከኢህአዴግ የባሰ ፀረ-ልማት አለ እንዴ?

ለዘመናት ዩራኒዩም (uranium) ከብር ማዕድን የሚገኝ አላስፈላጊ ተረፈ ምርት ተደርጎ ይወሰድ ነበር። የዩራኒዩም የቀድሞ መጠሪያው “pitchblende” ሲሆን ቃሉ “pechblende” ከሚለው የጀርመንኛ ቃል የመጣ ነው። በጀርመንኛ “pech”ማለት ደግሞ አላስፈላጊ የሆነ ውዳቂ ነገር (failure, nuisance) እንደማለት ነው። በዚህ መልኩ አላስፈላጊ ተረፈ-ምርት ተብሎ ሲጣል የነበረ ማዕድን በ1930ዎቹ ከፍተኛ የኃይል ምንጭ ለመሆን በቃ። ለረጅም ዘመናት እንደ ተራ ውዳቂ ሲቆጠር … Continue reading ከኢህአዴግ የባሰ ፀረ-ልማት አለ እንዴ?

በመንግስት ትዕዛዝ እንጂ በፌስቡክ መረጃ የሞተ ሰው የለም!

አንድ መሪ በየትኛውም መድረክ ቢሆን የሚናገረው ነገር ሀገርና ሕዝብን ወክሎ እንደመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል። ከዚህ ቀደም፣ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በሀገሪቱ የተከሰተውን ግጭትና አለመረጋጋት አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” የሚለውን ዓ.ነገር በመናገር ብቻ እንዴት በህዝብ ላይ ጦርነት እንደ አወጁ ተመልክተናል። አሁንም ጠ/ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር … Continue reading በመንግስት ትዕዛዝ እንጂ በፌስቡክ መረጃ የሞተ ሰው የለም!

“ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ” ሲባል አፌን ኩበት…ኩበት ይለኛል 

እኔ የምለው... ከእናንተ ውስጥ የኢትዮጲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) (EBC) የሚመለከት አለ? ካላችሁ የከበረ ሰላምታዬን አድርሱልኝ። እሱን መመልከት ካቆምኩ ሦስት አመት ይሆኛል። ይህን ያህል ከኢብኮ ጋር ያቆራረጡኝ "ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ" በሚሉት ቃላት ናቸው። ላለፉት አስር አመታት እንደነዚህ ቃላት ለዛና ትርጉም ያጣብኝ ቃል የለም። በዜና እወጃ፣ በባለስልጣናት መግለጫ ወይም በተመልካቾች አስተያየት መስጫ፤ “ሰላም፥ ልማት፥ ዴሞክራሲ” የሚሉትን ቃላት … Continue reading “ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ” ሲባል አፌን ኩበት…ኩበት ይለኛል 

የኦህዴድ ተሃድሶ፡ ከማሳደድ ወደ ማውረድ

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ሁለት ከፍተኛ አመራሮቹን፤ የፓርቲው ሊቀመንበርና የክልሉ ፕረዘዳንት የነበሩትን አቶ ሙክታር ከዲር እና ምክትል ሊቀመንበር የነበረችውን ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከኃላፊነት ማውረዱ ተገልጿል። በምትኩ አቶ ለማ መገርሳን ሊቀመንበር እና ዶ/ር ገበየሁ ወርቅነህን በም/ሊቀመንበርነት መርጧል። ኦህዴድ/ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮቹን ከኃላፊነት ማውረዱ በድርጅቱ ውስጥ “ተሃድሶ” እየተካሄደ ስለመሆኑ ይጠቁማል?  ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት ለመውረድ ለማዕከላዊ ኮሚቴ … Continue reading የኦህዴድ ተሃድሶ፡ ከማሳደድ ወደ ማውረድ

ኢህአዴግ ካልታደሰ አይወድቅም

አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች “ኢህአዴግ በቅርቡ ይወድቃል” ሲሉ፣ ደጋፊዎቹ ደግሞ “በቅርቡ ይታደሳል” እያሉ ይገኛል። ከመቼውም ግዜ በላይ በሀገሪቱ ፖለቲካ ለውጥ ስለማስፈለጉ ግን ሁለቱም ወገኖች አምነው የተቀበሉት ይመስላል። ይህ ለውጥ ደግሞ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከኢህአዴግ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። የሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንደ መንግስት በኢህአዴግ ላይ ውድቀት ወይም ተሃድሶ ሊያስከትል ይቻላል። ታዲያ እዚህ ጋር ቁልፉ ጥያቄ … Continue reading ኢህአዴግ ካልታደሰ አይወድቅም

ኢህአዴግ፡ ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ!

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህብረሰብ ሊሰጥ የታቀደው ስልጠና ዛሬ ላይ ተጀምሯል። ለስልጠናዉ ከተዘጋጁ ሰነዶች ውስጥ የመጀመሪያው “የሩብ ምዕተ ዓመታት የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጉዞ…” የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። በመረሃ-ግብሩ መሰረት ጠዋት ላይ በአሰልጣኞቹ ገለፃ ሲሰጥ እንደተለመደው በአሰልጣኝነት የተመደቡት የመንግስት ኃላፊዎች ለታዳሚው የሚመጥን ስልጣና ለመስጠት የአቅምና ክህሎት ችግር እንዳለባቸው በግልፅ ያስታውቃል። ይህ ግን ላለፉት አስር አመታት የታዘብኩት … Continue reading ኢህአዴግ፡ ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ!

ልማት የሕዝብ ነው፣ መንግስት ጥገኛ ነው

አብዛኞቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሀገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ልማትና እድገት እያስመዘገቡ እንደሆነ ያስባሉ። ነገር ግን፣ እነሱ እንደሚሉት በሀገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ልማትና እድገት እያስመዘገቡ አይደለም። ይሄን ያልኩበት ምክንያት “ኢህአዴግ ልማት አምጥቷል/አላመጣም” ወደሚለው ጉንጭ-አልፋ ክርክር ለመግባት ፈልጌ አይደለም። የኢህአዴግ መንግስት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ሁሉም መንግስታት በራሳቸው የልማትና እድገት ምንጭ ሊሆኑ አይችሉም። ምክንያቱም መንግስት በሀገር ልማትና እድገት ውስጥ ከደጋፊነት የዘለለ … Continue reading ልማት የሕዝብ ነው፣ መንግስት ጥገኛ ነው

አመፅ የማን ልጅ ነው፡ የልማት ወይስ የአምባገነንነት?

በተለያዩ አከባቢዎች አመፅና ተቃውሞ ሲነሳ አንዳንድ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የሀገሪቱ ልማት ያስከተለው ችግር እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣል። በእርግጥ የሀገር ልማት ለአመፅና አለመረጋጋት መንስዔ ሊሆን ይችላል? አመፅ የልማት ወይስ አምባገነንነት ተግባር ውጤት ነው? በዚህ ፅሁፍ እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን በዝርዝር እንመለከታለን። በቅድሚያ ልማት ምንድነው የሚለውን በአጭሩ መመልከት ያስፈልጋል። ልማትን “ሰላም፥ ጤና፥ ትምህርት እና መሰረተ-ልማት” በማለት በአጭሩ መግለፅ ይቻላል። … Continue reading አመፅ የማን ልጅ ነው፡ የልማት ወይስ የአምባገነንነት?