ምህረት: በፀረ-ሽብር ሕጉ መከሰስ ወይም መሰረዝ ብቻ ይገኛል!!

የዜጎች መብት፤ ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የጠየቁ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች፣ በአጠቃላይ መብትና ነፃነትን የጠየቁ በሙሉ ‹‹ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ›› በሚል በፀረ-ሽብር ሕጉ እየተከሰሱ፣ እየታሰሩና እየተሰደዱ ባለባት ኢትዮጲያ ውስጥ ይህን የፀረ-ሽብር ሽብር ከማስወገድ ወይም በአሸባሪነት ከመከሰስ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም፡፡

ስለዚህ፣ ዘወትር የዜጎቾች ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በመጮኽ የፀረ-ሽብር ሕጉን እጥሳለሁ፡፡ በዚህም፣ ወይ በአሸባሪነት እከሰሳለሁ፣ ወይም የፀረ-ሽብር ሕጉ እንዲሰረዝ አደርጋለሁ፡፡ በፀረ-ሽብር ሽብር ውሰጥ፤ ያለፍትህ ምህረት ነፃነት የሌለው መብት ነው፡፡