ወሊሶ: የግብር ጭማሪ ያስነሳው አድማ ለ2ኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል!

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ከግብር ጭማሪ ጋር በተያያዘ የተነሳው አድማ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዉሏል። በከተማ ውስጥ ሆቴሎች እና የንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የለም። የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ በእግር ነው የሚንቀሳቀሱት።

አዲሱን የግብር ተመን በመቃወም በወሊሶ ከተማ እየተካሄደ ባለው አድማ የሕዝብ ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡

ከትላንትነው በተለየ በዋናው አስፋልት ላይ በሚያልፉ መኪኖች ላይ ጥቃት እየተፈፀመ አይደለም። ቁጥራቸው ከወትሮው ያነሰ ቢሆንም የሕዝብና የጭነት ተሸከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ በሰላም እያላፉ ይገኛሉ። የኦሮሚያ አድማ በታኝ ፖሊሶች አሁንም ከተማውን ፓትሮል (Patrol) በማድረግ ላይ ይገኛሉ። መሃል ከተማ የሚገኙ ትራፊክ ፖሊሶች የከተማው መናህሪያ (bus station) ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ለመንገደኞች በማሳወቅ ላይ ይገኛሉ።

የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ባንኮች ክፍት ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ከዚህ በተረፈ የግል ቢዝነስ ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ሱቆች፣ በከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ባለ ሶስት ጎማ ተሸከርካሪዎች (ባጃጆች) ለሁለተኛ ቀን አገልግሎት እየሰጡ አይደለም። በከተማው የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች እና የመንግስት ኃላፊዎች የንግድ ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ አያስገድዱም። 

ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በተለየ መልኩ ወጣቶች የንግድ ቤቶች፣ ሆቴሎችና የሕዝብ ማጓጓዣዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ አያስገድዱም። በትላንትናው ዕለት በድንጋይ ጥቃት ከተፈፀመባቸው መኪኖች በስተቀር የኃይል ጥቃት የደረሰባቸው የንግድ ቤቶች እና ተቋማት አልተመለከትኩም። ከዚህ አንፃር፣ ጥያቄው በዋናነት የንግዱ ማህብረሰብ ጥያቄ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። 

በትላንትናው ዕለት የክልሉ ልዩ ፖሊስ አባላት ሁለት ወጣቶችን ይዘው ሲወሰዱ ተመልክቼያለሁ፡፡ የተወሰኑ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን እንደዚሁ ታዝቤያለሁ፡፡ በአጠቃላይ፣ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አንፃር ሲታይ የአሁኑ ፍፁም ሰላማዊ ሊባል የሚችል ነው፡፡

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s