​የሕዝብን ጥያቄ ማጣጣል ራስን ጠልፎ መጣል ነው!   

በእነ አንቶኔ ቤት በስርዓቱ ላይ አደጋ የሆነ ለውጥ በመጣ ቁጥር የመጀመሪያ ስራቸው ማጣጣል እና ስም ማጥፋት ነው። ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ ብአዴን ወይም ኢህዴድ እነሱ የማይፈልጉትን አቋም ካንፀባረቁ የፓርቲውን አቋም ማጣጣል፣ የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ስም ማጥፋት ይጀመራል። 

ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በብአዴን እና በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ የተከፈተው የሰም ማጣፋት ዘመቻ ልብ ይሉዋል። ለምሳሌ ከሰሞኑ የጠ/ሚ “ፕሮቶኮል ኃላፊ አሜሪካ ሄደው ከዱ” ሲባል ግለሰቡን አንዴ” አትክልተኛ፥ ሻይ አፍይ፥ …ወዘተ” የስም ማጥፋት (character assassination) ዘመቻ ተከፈተባቸው። ኤርሚያስ ለገሰ ጥሏቸው ወደ አሜሪካ ሲኮበልል እነ ዘፅዓት አናኒያ “ድሮም እኮ የብአዴን ተላላኪ ነው” እያሉ ማሽሟጠጥ ጀመሩ። ከፍተኛ ባለስልጣናትን ቀርቶ ተራ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ስም የሚያጠፉ ተራ ተሳዳቢዎችን በፌስቡክ እንዳሰማሩ ይታወቃል። 
ሰሞኑን አባዱላ ገመዳ ከአፈ-ጉባዔነት በመውረዱ ምን እንዳሉ አልሰማሁም። ዛሬ በወሊሶ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ግን ሰልፈኞች ለአባዱላ ገመዳ እና ለአዲሱ የኦህዴድ አመራሮች አድናቆትና ድጋፋቸውን ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ሰልፈኞቹ ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ መፈክሮች አሰምተዋል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የህወሓት/ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን በስም እየጠሩ “የስኳር ሌባ!” ሲሉ ሰምቻለሁ። ከዚህ በተጨማሪ፣ “የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት “ወያኔ” እንጂ አማራ አይደለም!” የሚል ሰምቼያለሁ። 

በዛሬው ዕለት በወሊሶ ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ (በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ፊት ለፊት)

Editከሰዓት በኋላ ደግሞ እነአንቶኔ እንደተለመደው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን ወሳኔዎች እና የተቃውሞ ሰልፉን በማጣጣል ላይ ተሰማርተዋል። በእርግጥ ገና ከጅምሩ ሲያጣጥሉት የነበረው ሕዝባዊ ንቅናቄ እንሆ ዛሬ ላይ እነሱን ሊጥላቸው ደርሷል። ነገር ግን፣ለምን ለውጥን እንደሚያጥላሉ እና የሰዎችን ስም እንደሚያጠፉ ፈፅሞ ሊገባኝ አልቻለም ነበር። 

ከፍተኛ መጠን ያለው ስኳር ያለ አግባብ ወደ ዉጪ መላኩ ያልገረማቸው ሰዎች “የስኳር ሌባ” እያለ የደረሱበት የሞራል ኪሳራ በይፋ ሲነገራቸው ከማፈር ይልቅ እውነቱን በማጣጣል የህዝቡን ሞራል ለመስለብ የሚያደርጉት ጥረት በጣም ይገርማል። በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ተሰሚነት ተሟጥጦ ቢያልቅም የሌሎችን ስም ለማጥፋት እረፍት ማጣታቸው ግራ ያጋባል። “ኧረ እንደው ይሄ ነገር ስም ይኖረው ይሆን?” ጎግል ላይ “Moral Corruption and character assassination” የሚሉትን ቃላት ፅፌ ስፈልግ “The social Unconscious in Persons, Groups and Societies” በሚል ርዕስ የቀረበ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ መጀመሪያ ላይ ወጣ። የሚከተለው አንቀፅ ከፅሁፉ ውስጥ የተወሰደ ነው፡- 

“Moral Corruption and character assassination occurred frequently in a political and social groups in the totalitarian state… This process is created and reinforced fear of authority and the system, which is destructive to individual integrity and human dignity and forced the people into helplessness and compliance with the regime.” The social Unconscious in Persons, Groups and Societies, Vol. 2. 

ከላይ የተጠቀሰውን ፅኁፍ እንዳነበብኩ “ለዚህ ነው ላከ!” አልኩ። በሙስና እና አድሏዊ አሰራር ውስጥ የተዘፈቀ ጨቋኝና አምባገነን የሆነ የፖለቲካ ቡድን እና ደጋፊዎች የሌሎችን እንቅስቃሴ በማጣጣል፥ በማጓጠጥ፥ በመሳደብ፥ በማስፈራራት እና የሰዎችን ስም በማጥፋት ላይ የተሰማሩት ለካስ ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ሆኖ ነው። ለካስ ዘወትር ጠዋት ማታ፣ ነገሮችን ሲያጥላሉና የሰው ስም ሲያጠፉ የሚውሉት የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ከድርጅቱ እንዳይወጡ ለማስፈራራት፣ ሕዝቡም የለውጥ እንቅስቃሴውን ተስፋ ቆርጦ እንዲተው ኖሯል። 

እነዚህ ወገኖች የለውጥ እንቅስቃሴን የሚያጣጥሉት እና የግለሰቦችን ስም የሚያጠፉት ሕዝቡውን ተስፋ በማስቆረጥና በማስፈራራት ለጨቋኙ ስርዓት ተገዢ እንዲሆን ነው። ብደልና ጭቆናን ተቀብሎ እንዲኖር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስታዊ ስርዓቱ ጨቋኝና አምባገነን ስለመሆኑ ማረጋገጫ እየሰጡ ነው። ስለዚህ አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ለማጣጣልና ለማንኳሰስ ሲጣደፉ ለምን እንደሚያደርጉት አውቆና ንቆ መተው ተገቢ ነው።        

ችግሩ በአብዛኛው የሚስተዋል በህወሓት/ኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ነው። “ታዲያ ይህ አካሄድ ህወሓትን ያዋጣል ወይስ አያዋጣውም?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ እንደ ችግሩን እንደ መፈለግድ ከባድ አይደለም። አንድ የፖለቲካ ቡድን የለውጥና መሻሻል ጥያቄን በማጣጣልና በስም ማጥፋት ለመግታት መሞከር ከጀመረ ራሱን ጠልፎ እየጣለ ነው። ምክንያቱም፣ የለውጥ ጥያቄ ተፈጥሯዊና አይቀሬ ነው። እንዲህ ያለ ፀረ-ለውጥ አቋም ይዞ በስልጣን መቆየት የተፈጥሮ ሕግን እንደ መቀየር ነው። የተፈጥሮ ሕግን ይቀበሉታል እንጂ አይቀይሩትም። በተመሳሳይ የለውጥ ጥያቄ ይቀበሉታል እንጂ አያስቆሙትም። በአጠቃላይ፣ የለውጥ ጥያቄን በማጣጣልና ስም በማጥፋት ማስቆም አይቻልም።

5 thoughts on “​የሕዝብን ጥያቄ ማጣጣል ራስን ጠልፎ መጣል ነው!   

  1. My fear is, due to the job done for the last 25 years the fate of EPRDF has closely tied with the fate of Ethiopia. EPRDF is almost dead before the people have a strong and genuine opposition party and national consensus. If, including EPRDF, building a nation wide opposition parties and bringing national consensus is not done within the coming couple of months, the disintegration of EPRDF would end up in the disintegration of the country (devil’s ear be deaf).

    Like

  2. Really accepted comment and idea. but one thing to say is is really TPLF take lead even today. it seems during Meles but currently OPDO and ANDM are the lead. so we need change but peacefully. the problem with EPRDF is still not establish democratic system in the party, institutions and others.so please accept free democratic election, make environment equal for all competitive and accept vote/voice of the nation.

    Like

  3. የወያኔ መንግስት ብነገረው የማይገባው ድንጋይ ራስ ሆኖ እንጂ በኢዲሞክራሲ ስርአት አልገዘም ያለውን ሰፊ ህዝብ በጠመንጃ አፈሙዝና ስም ማጥፋት ለማስተዳደር መሞከር ትልቅ ክሳራን የሚያስከትል እና የሞኞች ሞኝ መሆን ይመስላል

    Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡