“የኦሮሞና አማራ ትብብር አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው!”

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ስዩም ተሾመ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ሳይታክቱ ፖለቲካዊ ሀሳቦቻቸውን በማካፈል ይታወቃሉ። መምህር ስዩም ከቃሊቲ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ከሰሞኑ የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሆነው የኦሮሞ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦ.ህ.ዴ.ድ) የሚታየው አዳዲስ ሁኔታዎች የምን መገለጫዎች ናቸው? ወቅታዊ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ወይስ ውስጣዊ የአስተሳሰብ ለውጥ?” በሚል አርስት ዙሪያ ተወያይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ይህን “የአንድ_ነን፣ አንለያይም…” የሚሉ ስሜቶች ባለቤት ማን ነው? ህዝቡ ወይስ ፓርቲው? የሀገሪቱ ህዝብ ሁለት ሶስተኛውን የያዙት አማራና ኦሮሞ አንድ ነን ሲሉ በሌላ በኩል የሚሰማው ድምጽ የምን ድምጽ ነው? ለምን? በኦ.ህ.ዴ.ድ ውስጥ የታየው የህዝባዊ አንድነት መንፈስ ወደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ፓርቲዎች ይጋባል ወይስ …? ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው? በእነዚህና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ይህን ማያያዣ (link) በመጫን እንድታዳምጡ ተጋብዛችኋል፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=Be83LKm8wnM&sns=em 

2 thoughts on ““የኦሮሞና አማራ ትብብር አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይ ነው!”

  1. Already millions of Amharas which are more than Amharas in Gojjam and Gonder have been living in Oromiya. What the hell the woyane puppet Lema Megarsa and Gegu is trying to do? These pupet leaders are not even elected by their peoples

    Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡