​“ወደ ቂሊንጦ ሲገቡ የአካል ጉዳቱ አልነበረም! ድብደባ መሆኑን ግን አላረጋገጥኩም” የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

በእነ ብስራት አበራ አበበ /20 ሰዎች/ የቀረበውን የሰብዓዊ መብት ጥስት አቤቱታን አስመልክቶ የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ባለ ዘጠኝ (9) ገፅ የምርመራ ውጤት ሪፖርት አቅርቧል። 

በአቤቱታ አቅራቢዎቹ በሸዋ ሮቢት በነበረው የምርመራ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው መናገራቸውን ተከትሎ ኮሚሽኑ ባደረገው የአካል ምልከታ፤ በሀይሩ ጀማል አብራር፣ በግዛቸው አበራ ወ/ጊዮርጊስ፣ ኤፍሬም ገቢሳ፣ ደምስ አልቤን ቱፋ እና አፍሬም ታደሰ አበበ የእጅና የጣት “ስብራት” መኖሩን፣ በኤፍሬም ሙላቱ መንግስት፣ መንተስኖት ኃይለማሪያም ገብሬ እና ዋስየሁን ደሳለኝ መኮንን ላይ ደግሞ በእግራቸው ላይ “ጠባሳ” መኖሩን፣ እንዲሁም በይርጋለም ሰብስቤ ያደቴ ላይ ደግሞ በግንባሩ ላይ “ጠባሳ” መገኘቱን በሪፖርቱ ገልጿል። ኮሚሽኑ ከታራሚዎቹ የግል ማህደር ጋር በማመሳከር ከላይ የተጠቀሱት የአካል ምልክቶች ግለሰቦቹ ወደ ማረፊያ ቤቱ ሲገቡ ያልተመዘበ መሆናቸውን አረጋግጧል። በመጨረሻም፣ በሪፖርት መሰረት፦ 

“ይሁንና እነዚህ አካላዊ ምልክቶች በምን ምክንያት በግለሰቦቹ ላይ ሊኖሩ እንደቻሉ የወንጀል ምርመራ እና የሕክምና ምርመራ በማድረግ ውጤቱ መታወቅ አለበት።…በመሆኑም አሁን ላይ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ወይም አልተፈፀመባቸውም የሚል ድምዳሜ መስጠት አስቸጋሪ ሆኖ ተገኝቷል” በማለት ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል። 

የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት የላከውን ባለ ዘጠኝ (9) ገፅ የምርመራ ውጤት ሙሉ ሪፖርት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የማውረጃ ማያያዣ (Download Link) በመጫን ማውረድና ማንበብ ይቻላል። 

የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምርመራ ውጤት ሪፖርት (Pdf)    

   
   

One thought on “​“ወደ ቂሊንጦ ሲገቡ የአካል ጉዳቱ አልነበረም! ድብደባ መሆኑን ግን አላረጋገጥኩም” የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡