​በ16 እስረኞች ላይ በምርመራ ወቅት የደረሰ ጉዳት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የክስ መዝገብ በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ የተከሰሱ 16 እስረኞች ላይ በምርመራ  ወቅት የደረሰባቸውን ጉዳት በሪፖርቱ አኳትቷል። በዚህም መሰረት:_

 1. ከበደ ጨመዳ: ቀኝ እጅ ላይ ትንሽ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር አውራ ጣት ስብራት፣
 2. ኢብራሂም  ካሚል: ቀኝ  እግር ላይ ጠባሳ፣  ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር ምልክቶች
 3. አግባው ሰጠኝ: ግራ ታፋ ላይ ሰፊ ጠባሳ፣ ቀኝ እግር ላይ ጠባሳ፣ ግራ እግር ላይ በሚስማር የተመታ  ምልክት፣ ጀርባ ላይ የግርፋት የሚመስሉ ምልክቶች
 4. ቶፊቅ ሽኩር: ቀኝ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የሁለት እግር አውራ ጣት ጥፍር መነሳት፣ ግራ እጅ ጠባሳ
 5. ሸምሱ ሰይድ:  የጀርባ የግርፋት የሚመስሉ ምልክቶች
 6. ሚስባህ ከድር: የካቴና የእስር ምልክቶች፣ ቀኝ እጅ ላይ ሰፊ ጠባሳ፣ ግራ እጅ ላይ አነስተኛ ጠባሳ፣ ቀኝ እና ግራ ታፋ ላይ  ጠባሰ፣ የግራ እጅ ጠቋሚ ጣት ስብራት
 7. ፍፁም ጌታቸው:  የቀኝ እጅ ጉዳት
 8. ተመስገን ማርቆስ: የቀኝ እጅ ስብራትና ጠባሳ፣ ሁለቱም እግሮች ሰፋፊ   ጠባሳዎች
 9. አሸናፊ መለሰ: የቀኝ እና ግራ ታፋ ላይ ጠባሳዎች፣ የግራ እጅ የቀለበት ጣት ስብራት
 10. ካሳ መሃመድ: ቀኝ እጅ ጥልቅ ጠባሳ፣ ጭንቅላት ላይ የመፈንከት ምልክት
 11. ሲሳይ ባቱ: ቀኝ እጅ ላይ ጠባሳና የጠቆረ ምልክት
 12. አቡዱልደፋር አስራት: ቀኝ እና ግራ እግር አውራ ጣት ጥፍር መነቀል
 13. ደረጀ መርጋ: ግራ እግር ላይ ስድስት ጠባሳዎች፣ ሁለቱም እጅ ላይ  ካቴና እስር የጠቆሩ ምልክቶች
 14. ቶፊክ ፈርሃ: ግራ እጅ ላይ ጠባሳ፣ የካቴና እስር የጠቆሩ ምልክቶች
 15. ኡመር ሀሰን: የግራ እግር አውራ ጣትና የቀኝ እግር ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣት ጥፍር መነቀል
 16. ሰይፈ ግርማ: ከጀርባ ትክሻ በግራ በኩል በሚስማር የተመታ ጠባሳ፣ ሁለቱም እግሮች ላይ ጠባሳ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሙሉ ሪፖርት ቀጥሎ ያለውን ማያያዣ በመጫን አውርዶ ማንበብ ይቻላል፡፡ 

ሙሉ ሪፖርት (Pdf)