ተከሳሾች በዳኞች ላይ ተቃውሞ በማቅረባቸው ከ3-6 ወር በሚደርስ እስራት ተቀጡ! 

​አስቻለው የተባለ ተከሳሽ ሱሪውን አውልቆ በምርመራ ወቅት የተኮላሸውን ብልቱን በችሎት አሳይቷል።  

በእነ ተሻገር ወልደሚካኤል ክስ መዝገብ እስረኞች አቤቱታ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ሲያቋርጥ የሚናገረው ተከሳሽ ሀሳቡን እንዲጨርስ የተናገረ ሌላ ተከሳሽ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከተቀመጠበት ወጠቶ ወደ ችሎቱ እንዲቀርብ ተደርጓል።
ተከሳሹ እንዲወጣ ሲጠየቅ ሌሎች ተከሳሾች “እኛም እንወጣለን” ብለው ተቃውሞ አሰምተዋል። መሃል ዳኘው መጀመርያ ” እንደሱ ከሆነ በሁላችሁም ላይ ቅጣት እንሰነዝራለን” ብለው የነበር ቢሆንም ተከሳሾቹን ለማረጋጋት ሞክረዋል።

ሆኖም  የግራ ዳኛው “አሁንም ይውጣ” ብለው ተከሳሹ ከወጣ በኋላ ተከሳሹን “ምንድን ነው የሚያወራጭህ?” በማለታቸው ተከሳሾቹ ተቃውሟቸውን በጩኸት ገልፀዋል። የግራ ዳኛውን ” ስነ ስርዓት ያዝ! “ሲሉም ተደምጠዋል። “ዳኛ ዘርዓይ ከሰባራ ባቡር ወደዚህ የመጣው እኛን ሊበቀል ነው!” ብለዋል። 

” እኛ የተከሰስነው አማራ በመሆናችን ነው። ልንሞት ነው የመጣነው። እንሞታለን” ብለዋል። በተቃውሞው ምክንያት ዳኞች ችሎት ጥለው ወጥተዋል።


አሁን ዘግይቶ በደረሰን መረጃ መሠረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ክስ መዝገብ በአራት ተከሳሾች ላይ ችሎት በመድፈር ወንጀል ፈርዶባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ ተሻገር ወ/ሚካኤል 3ወር እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ በለጠ አዱኛ፣ 8ኛ ተከሳሽ ተስፋሚካኤል አበበ እና 9ኛ ተከሳሽ እንዳለው ፍቃዴ  6 ወር ተፈርዶባቸዋል።

እነ ተሻገር ወልደሚካኤል የፀረ ሽብር አዋጁ እና የወንጀለኛ መቅጫው በሚለው መሰረት ወንጀል ተሰራበት በተባለው አካባቢ እንዲዳኙ አቤቱታ አቅርበዋል። አቤቱታውን በሚያቀርቡበት ወቅት ዳኞቹ በማቋረጣቸው ተከሳሾች ፍ/ቤቱ  አቤቱታችን  ሊሰማ ይገባል ብለው ተቃውሞ  አሰምተዋል። ችሎት ተቋርጦ ተከሳሾች ከወጡ በሁዋላ ተመልሰው እንዲገቡ ተደርጎ  በችሎት መድፈር ተፈርዶባቸዋል።

One thought on “ተከሳሾች በዳኞች ላይ ተቃውሞ በማቅረባቸው ከ3-6 ወር በሚደርስ እስራት ተቀጡ! 

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡