“ኢብኮ (METEC) የድንጋይ ከሰል የመሸጥም ሆነ የማስተላለፍ ህጋዊ ፍቃድ የለውም!” የኦሮሚያ ውሃ ሃብት ቢሮ

ህገ-ወጥ የሆነ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር በድብቅ ቢፈጸምም፣ ከብዙሀኑ ህዝብ እይታ ግን ፈጽሞ ሊሰወር አይችልም! (በኦሮሚያ ውሃ ቢሮ የተሰጠ መግለጫ)


የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የክልሉ ህብረተሰብ ከመቼዉም በላይ በህገ-ወጥ መልኩ የማዕድን ሀብትን በመዝረፍ፣ በመሸጥና በማስተላለፍ ላይ የተሠማሩ ልማታዊ ያልሆኑ ባለ ሀብቶችም ላይ ሆነ ግለሰቦች ላይ እርምጃን የመዉሰድ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮረፖሬሽን በኢሉአባቦር ዞን ያዮ ወረዳ የኮል ፎስፌት ማዳበሪያን በማምረት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ 

ኮርፖሬሽኑም በተጨማሪ ለዚህ እንዳስትሪ ግብአት የሚሆነኝን የከሰል ድንጋይ ማዕድን በአጨቦ እና ወተቴ አከባቢዎች ከ2004 ጀምሮ በማምረት ላይ እገኛለሁ በማለት ከማዕድን ሚንስቴር  ወስጃለዉ የሚለዉ እንድ ገጽ ደብዳቤ ግልጸኝነት የሌለዉ፣ ምንም ዓይነት የስምምነት ሰነድ፣ ዶክሜንት ፕሮፖዛል፣ ህጋዊ የሮያሊቲ ክፍያ፣ የመሬት ኪራይ ግብር፣ ህጋዊ በሆነ መልኩ የመንግስትን ግብር የተከፈለበት በቂ ሰነድ ሳይኖረዉ  በመንቀሳቀሱና፣ 

ከዚህም ባሸገር ማዕድኑን የመሸጥም የማስተላለፍ ምንም ዓይነት ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረዉ የከሰል ድንጋይ ማዕድን ምርቱን ወደ ሌላ ቦታ በህገ ወጥ መልኩ ሲያዘዋዉር በመቆየቱ ህብረተሰቡ ባደረገዉ ጥቆማ  የክልሉ መንግስት ይህን ድርጊት በማስቆም ጉዳዩን በማጣራት ላይ ይገኛል፡፡

ይህም እንዳለ ሆኖ በቀጣዩም ክልሉ በህገ መንግስት የተፈጥሮ ሀብቱን የማስተዳደር በተሰጠዉ መብት በመጠቀም የአከባቢዉን ህብረተሰብ ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ማንኛዉም የሚመለከተዉ አካል ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም የኪራይ ሰብሳቢነትን ድርጊት በማስቆም ልማትን ማፋጠን ይጠበቅበታል፡፡