ፕረዜዳንቱ ወደ ውጪ፣ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ!!

የተማሪዎችን ጥያቄ ተቀብሎ ተገቢ ምላሽ መስጠት የዩኒቨርሲቲው ፕረዜዳንት ሥራና ሃላፊነት ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ በመምህራንና ተማሪዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ ተግባራዊ እንዲደረግ አመራር መስጠት የፕረዜዳንቱ ድርሻና ሃላፊነት ነው፡፡ በዚህ መሠረት፣ በአንድ በኩል ተማሪዎቹ ስለ መመሪያው ዓላማና ግብ በማሳወቅ ማሳመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጥያቄያቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር በማቅረብ መመሪያው ያለበትን ክፍተት መጠቆምና የተሻለ የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ 

ተማሪዎች ወደ አመፅና ተቃውሞ የሚሄዱት ፕረዜዳንቱ ይህን ማድረግ ስለተሳነው ብቻ ነው፡፡  ስለዚህ ግቢውን ለቅቆ መውጣት ያለበት የዩኒቨርሲቲው ፕረዜዳንት እንጂ ተማሪዎቹ አይደሉም፡፡ ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎቹ የመማሪያ ተቋም እንጂ የፕረዜዳንቱ የግል ንብረቱ አይደለም፡፡ ተማሪዎቹ Cost_Sharing ከፍለው ነው የሚማሩት፣ ፕረዜዳንቱ ደሞወዝ ተከፍሎት ነው የሚሰራው፡፡ ተማሪዎቹ አገልግሎት የማግኘት መብት አላቸው፣ ፕረዜዳንቱ አገልግሎት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 

የተማሪዎቹ የወደፊት እድላቸውን በሚወስን ማንኛውም ጉዳይ ላይ የመጠየቅ፥ የመቃወምና አቤቱታ የማሰማት መብት አላቸው፡፡ ፕረዜዳንቱ የተማሪዎቹን ጥያቄ ተቀብሎ ምላሽ መስጠት አለበት፡፡ ለተማሪዎቹ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ በመስጠት መብታቸውን ማክበርና ማስከበር የተሳነው ፕረዜዳንት ግዴታውን መወጣት ተስኖታል፡፡ የሥራ ድርሻውን መወጣት ያቃተው ፕረዜዳንት ያለው አማራጭ ራሱን ከሃላፊነት በማንሳት ዩኒቨርሲቲውን ለቅቆ መውጣት ነው፡፡ ተማሪዎቹ በአግባቡ ያቀረቡትን ጥያቄ መመለስ የተሳነው ፕረዜዳንት የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ግቢ ለቅቃችሁ ወጡ ማለት አይችልም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ እሱ ራሱ ቅጥር ግቢውን ለቅቆ መውጣት አለበት፡፡ 

ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ እንዲለቁ የተደረጉ ተማሪዎች ከከተማው ነዋሪዎች ምግብ ለምነው እየበሉ (ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ምስል)

በአጠቃላይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው ባለቤቶች ናቸው፣ ፕረዜዳንቱ ተቀጣሪ ደሞወዝኛ ነው፡፡ ሥራውን መስራት ካቃተው ግቢውን ለቅቆ መውጣት አለበት፡፡ ነገር ግን፣ እንዲህ እንደ ጅማ_ዩኒቨርሲቲ ፕረዜዳንት ተማሪዎችን ከግቢ አስወጥቶ በየሰው ቤት ምግብ ለምነው እንዲበሉ ካደረገ ግን ሥራ ከመልቀቅ በተጨማሪ #በወንጀል መጠየቅ አለበት፡፡

One thought on “ፕረዜዳንቱ ወደ ውጪ፣ ተማሪዎቹ ወደ ግቢ!!

  1. የዘንድሮ ተማሪ ይገርማል ….confidence የሌለው ተማሪ የመውጫ ፈተና አልፈተንም ማለት ምን ማለት ነው ይህ ለመምህራኑም መልእክት አለው ….ከተማሪው ብሶ አስተማሪው መፈተን የለባቸውም ይላል …እነርሱ የክፍል ስራ ሰተው ፌስ ቡክ ላይ ይጣዳሉ መች ያስተምራሉ…… የትምህርት ጥራት ቢረጋገጥ ኖሮ ሁሉም አይሸናም ነበር…….student centered ከመጣ ወድህ ሁሉም አንድ ላይ ደድበዋል……እውቀት ነጻ ያወጣል…..በሊብያ ከተሰደዱት almost 12% የመጀመሪያ ድግሪ አላቸው ያቅም ለ 2.75 በላይ አስመዝግበው…

    Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡