የፍርድ ቤት ውሎ ዘጋቢዎች ወደ ችሎት እንዳይገቡ ተከለከሉ! 

<<4ኛ ወንጀል ችሎት በር እንደቆምን 5:20 ሆኗል። ከአንድ እስረኛ በስተቀር ቀጠሮ ያላቸው እስረኞች “አንበሳ ግቢ (የእስረኞች መቆያ) ” ቁጭ ብለዋል። ፖሊሱ  እንዳንገባ ወደኋላ ይገፋናል። ዝግ ችሎት ነው ወይ ብለን ስንጠይቅ መልስ አይሰጡም።  አሁን ደግሞ ገብቶ የነበረው እስረኛም ጉዳዩን ጨረሰ መሰለኝ ወጥቷል።>> ጌታቸው ሽፈራው

<<4ኛ ወንጀል ችሎት ቀጠሮ የነበራቸው እስረኞች ወደ ችሎት አንገባም እንዳሉ ታውቋል። እስረኞቹ ወደ ችሎት አንገባም ያሉት በየመዝገብ ተለይተን በየተራ እንድንገባ ተደርገናል፣ በመዝገብ ተለይተን እየተጠራን መግባት የለብንም በሚል መሆኑን የፖሊስ ምንጮች ገልፀዋል።

ከአሁን ቀደም  ቀጠሮ ያላቸው በሁሉም መዝገቦች የተከሰሱ እስረኞች ወደ ችሎት ገብተው ጉዳያቸው  ይከታተሉ ነበር።  በዛሬው ችሎት እነ ሉሉ መለሰ፣ ኮንስታብል ደጋጋ ብርሃኑ፣  ማሙዬ ዲሮና በሌሎች መዝገቦች የተከሰሱ እስረኞች ቀጠሮ ነበራቸው።
እስረኞቹ ወደ እስር ቤት በሚመለሱበት ወቅት መኪናው ከወትሮው በተለየ የእስረኞች ማቆያው (አንበሳ ግቢ) ድረስ ተጥግቶ ወደ መኪና  እንዲገቡ ተደርገዋል። እስረኞቹ ወደ መኪና ሲገቡ ከቤተሰብ ጋር ሰላምታም እንዳይለዋወጡ ቤተሰብ ከአካባቢው እንዲርቅ ተደርጓል።>> ጌታቸው ሽፈራው

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው
Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s