ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ የሚመሰክሩ የአቃቤ ህግ ምስክሮች በአድራሻቸው አልተገኙም

መዝገቡ ለብይን ተቀጥሯል። 

የእነ ዶ/ር መረራ ጉዲና መዝገብ ለዛሬ የተቀጠረው 1ኛ ተከሳሽ በሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ የሚመሰክሩ ሁለት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር። አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማቅረብ አለማቅረቡን በሚጠየቅበት ወቅት ፤ ፖሊስ ምስክሮቹን በአድራሻቸው ፈልጎ ማግኘት እንዳልቻለ በደብዳቤ መግለፁን ጠቅሶ “ምስክሮቹን እኛም አንፈልጋቸውም። ከዚህ ቀደም በመሰከሩት ምስክሮች እና ባቀረብነው የሰነድ ማስረጃዎች ክሳችንን አስረድተናል ብለን ስለምናምን ሁሉም ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን እንዲሰጥልን” ሲል ጠይቋል። 

የዶ/ር መረራ ጠበቆች ብይኑ በሚሰራበት ወቅት ከዚህ ቀደም በመቃወሚያ ያነሷቸው ሃሳቦች ታሳቢ እንዲሆኑ የጠየቁ ሲሆን ዳኞችም በመቃወሚያው ላይ የተሰጠው ብይኖችን እንደሚያዩ ጠቅሰው፤ ውድቅ የተደረጉ ወይም የታለፉ መቃወሚያዎች ካሉ ግን ስነስረአት ህጉ ስለማይፈቅድ ወደ ኋላ መመለስ እንደማይቻል ገልፀዋል። 

ዶ/ር መረራ ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡበት ጊዜ እና ከፍርድ ቤት ወደ እስር ቤት በሚመለሱ ሰአት እጃቸው በካቴና መታሰር ከመቅረቱ ውጪ በማረሚያ ቤቱ ላይ ከዚህ ቀደም የቀረቡ አቤቱታዎች ፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሰረት ተፈፃሚ እየሆኑ እንዳይደለ የተከሳሽ ጠበቆች ገልፀዋል። ማረሚያ ቤቱ ከአንድ ጠበቃ ውጪ የተቀሩት ጠበቆች ደንበኛቸውን (ዶ/ር መረራ ጉዲናን) አግኝተው እንዳያማክሩ መከልከላቸውን፤ እንዲሁም ዶ/ሩን እንዲጎበኙ የተፈቀደላቸው ቤተሰቦች በቁጥር እና በስም ዝርዝር ውስን በመሆናቸው በዝርዝሩ ያልተካተቱ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ከተለያየ የአለም ክፍል እና ከሃገር ውስጥ ከተለያየ ቦታ እየመጡ መጠየቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል ጠበቆቹ። 

ዳኛውም ማረሚያ ቤቱ በአቤቱታው የተጠቀሱትን ድርጊቶች ለምን እንደሚያደርጉት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለማረሚያ ቤቱ እንደሚልኩ ገልፀዋል። 
መዝገቡን መርምሮ ብይኑን ለመስራት ለታህሳስ 25/2010 ቀጠሮ ተሰጥቷል።


ምንጭ፦ EHRP

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s