​እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ  የቂሊንጦ እስር ቤት ኃላፊን በዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሚጠይቋቸው ገለፁ

በእነ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ ስር የተከሰሱ እስረኞች የቂሊንጦ እስር ቤት ኃላፊን በዘር ማጥፋት ወንጀል  እንደሚጠይቋቸው ገልፀዋል። ዛሬ ታህሳስ 24/2010 ዓም   በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ የዐቃቤ ሕግ 83ኛ ምስክር ሆነው የቀረቡት የቂሊንጦ እስር ቤት ደህንነትና ጥበቃ ኃላፊ ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ ኣብርሃ ሊመሰክሩ በቀረቡበት ወቅት ከእስረኞቹ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

ተከሳሾቹ  ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም  በቂሊንጦ ቃጠሎ  ወቅት እስረኞችን በመግደልና በማስገደል እንዲሁም አስከሬናቸውን በእሳት በማቃጠል ተጠያቂ ናቸው ብለዋል። 1ኛ ተከሳሽ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ምስክር ሆነው የቀረቡትን  ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠይቋቸው በመሆኑ መመስከር እንደሌለባቸው ገልፆአል። 5ኛ ተከሳሽ አግባው ሰጠኝ ምስክሩ በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት ሰው ገድለው እሳት ውስጥ በመጨመር ወንጀል እንደፈፀሙ ለችሎቱ ገልፆአል። በተመሳሳይ 4ኛ ተከሳሽ  አበበ ኡርጌሳ  ምስክሩ ለችሎቱ  ጠቁመው ባሳዩት  ወቅት “ያውቀኛል። ሲገድልና ሲያስገድል የነበረ ሰው ነው። በዘር ማጥፋት ሊጠየቅ የሚገባው ሰው ነው” ብሏል። 33ኛ ተከሳሽ ሸምሱ ሰኢድ “ገድሎ ማዕረግ የተሰጠው፣ ዞን 5 የተባለ የድሃ ልጅ የሚሰቃይበት እስር ቤት ያሰራ ሰው ነው።” ሲል ዋና ኦፊሰሩ እንዳይመሰክሩ ተቃውሟል።  በተጨማሪም 31ኛ ተከሳሽ ጌታቸር እሸቴ “ምስክሩ ህሊናቸውን የሸጡ ናቸው። እንደሳቸው ህሊናቸውን የሸጡ አሉ። መንግስት ጨፍጭፌያለሁ ብሎ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ እንኳን ከስህተታቸው አልተማሩም” ብሏል።

ተከሳሾቹ ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ እንዳይመሰክሩባቸው ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ፣ 18ኛ ተከሳሽ አንጋው ተገኘ “እኛ ፍትህ እናገኛለን ብለን ሳይሆን ለታሪክ እንዲመዘገብ ስለምንፈልግ ይመስክር” ብሏል። ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ  ዋና ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ እንዲመሰክሩ ተከሳሾቹን ካግባቡ በኋላ ተከሳሾች ምስክርነቱ እንዲቀጥል ተስማምተዋል።

በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ 38ቱ ተከሳሾች
Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s