​የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን አጠናቀቀ 

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ10 ቀናት በአዳማ ስብሰባውን ሲያካሂድ የቆየው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን አጠናቋል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው በቆይታው ውስጠ ዴሞክራሲን ለማጎልበት፣ አንድነትን ለማጠናከር እና የአመራር ስብዕናን ለማጠናከር በጥልቀት ሲወያይ መቆየቱን ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። 

በኢህአዴግ ምክር ቤት 14 አባላቱን ተጠያቂነትን ለማስፈን እና የተሻለ ትግልን ለማካሄድ በአዳዲስ ጠንካራ አመራሮች መተካቱንም ነው ያስታወቀው።

አራት የማዕከላዊ ኮሚቴው አባላት እስከ ቀጣዩ ድርጅታዊ ጉባኤ ድረስ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፥ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልንም በማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ መወሰኑን አስታውቋል።


ምንጭ፦ FBC 

One thought on “​የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ስብሰባውን አጠናቀቀ 

 1. የአገራችን ችግር ምንጩ በቅድሚያ ህወሓት ነው። ቀጥሎ፣ የህወሓትን ስውር ደባ መቋቋምና ሕዝቡን በአገራዊ ራእይ ዙሪያ ማስተባበር የቻለ መሪ አለመገኘቱ ነው። በመጨረሻም፣ አድሎአዊ አስተዳደር ነው። ከላይ የተዘረዘረው የሥልጣን ሽሚያ ያመለክታል። ሆኖም ሥልጣንና ጥቅም በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ብቻ አይደለምና፣ በየሚንስቴር መ/ቤት፣ በሁሉም ደረጃ ይፋ ተደርጎ ይህን ለማስቆም ብሔራዊ አካል መቋቋም ይኖርበታል። በአየር መንገድ። በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር። ወዘተ። በኢትዮጵያ ስም በዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በየቆንስላዎች ብቃት ያለው ዜጋ ሳይወዳደር የህወሓት ሰዎች ብቻ መመደባቸው መቆም አለበት። ቴድሮስ አድሃኖም፣ ሙሉ ቀጸላ፣ ሐዲስ ታደሰ፣ መሐሪ ታደሰ፣ አበበ አእምሮ ሥላሴ፣ ወዘተ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለውድድር እድሉ ሳይሰጣቸው የተሾሙ ናቸው። ብቃት ካለውና ለሌላውም እድሉ እስካልተነፈገ ትግሬ አማራ ኦሮሞ መሆን ቁምነገር አይደለም። ቴድሮስ ጤና ጥበቃና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የሆነው በችሎታና በልምድ ከርሱ የላቁ ጠፍተው አይደለም። የዓለም አቀፍ ጤና ዳይሬክተርነቱን ለማግኘት ከመንግሥት ካዝና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶ ነው።
  በቤንሻንጉል ጉሙዝ ለምሳሌ፣ በአማራ ወይም በኦሮምያ ክልል ኗሪ የሆነ ንግድ መክፈት አይፈቀድም። ለትግራይ ኗሪ ግን ይፈቀዳል። ማንም ትግራይ ሄዶ ንግድ ማቋቋም አይችልም። ይኸ መቅረት ይገባል። በአሁኑ ወቅት በተለይ ከ18 ዓመት ወዲህ ብዙ የትግራይ ተወላጆች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ኢኮኖሚውንና ፖለቲካውን ተቆጣጥረውታል። ይህ መቆም አለበት። ለሁሉም እኩል እድል መሰጠት አለበት። በጋምቤላም ይኸው ነው። ጥቅም ባለበት ሁሉ። የአካባቢው ኗሪ ግን ከነበረበት ብዙም ፈቅ አላለም። የሚገርመው፣ የትግራይ ተወላጆች የሰበሰቡትን ሃብት እዚያው ክልል እንደማልማት ትግራይና አዲስ አበባ ቤት ይሠራሉ፣ ወደ ውጭ በውጭ ምንዛሪ ያሸሻሉ። ሥራ ፈጥረናል ይላሉ፤ ከሚያሸሹት ሃብት አንጻር ይኸ ኢምንት እንደ ሆነ መገመት አያዳግትም።
  አንዳንድ ሰዎች፣ ይህማ አንድ ዘር (ትግራይን) መጥላት ነው ይላሉ። አይደለም። በዘር አስተዳደር ክልል የጀመረው ህወሓት መሆኑን አንርሳ። ስለዚህ እርሱ ባመጣው አሠራር መጫወት ተገቢ ነው። የትግራይን ሰው መጥላት ልክ አይደለም። ማንንም በጎሳው የተነሳ መጥላት አግባብ አይደለም።
  ሰላም አውቶቡስ እንመልከት። ድሮ አንበሳ አውቶቡስ በደንብ ከተማውንና ክፍለ ሃገሩን ያዳርስ ነበር። ህወሓት የክፍለ ሃገሩን አስቁሞ በራሱ ድርጅቶች በኩል ተቆጣጠረው። ሰላም አውቶቡስ የሚገጣጠመው በሜቴክ ነው። ሜቴክ ሌላ የህወሓት ድርጅት ነው። መሆን ያለበት፣ ቢያንስ ቢያንስ፣ ሰላም አውቶቡስ ወደ አማራ ክልል ወይም ኦሮምያ፣ ወይም ቤንሻንጉል መስመር ሲሠማራና ክልሉን ሲሻገር ለአውራ መንገዱ ቀረጥ መክፈል ይኖርበታል፤ የክልሉ ኗሪዎች በሾፌርነት፣ በቲኬት ቆራጭነት መቅጠር ይገባል።
  ህወሓት የሚደጋግመው ተረት አለው። ከደርግ እሥራት መስዋእት ከፍዬ ሕዝቡን ነጻ ያወጣሁት እኔ ነኝ እያለ። ስድሳ ሺህ የሚደርስ የትግራይ ወጣት መስዋእት አድርጌ ይላል። እውነት ነው? ስንቱ የትግራይ ወጣት በህንፍሽፍሽ እና ከትግራይ ሊግ፣ ከሻቢያ፣ ከጀብሃ፣ ከኢሕአፓ ጋር በተካሄደው የርስበርስ ጦርነት ተማገደ? ደግሞስ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ሳይሆን ለትግራይ ሪፑብሊክ ሲዋጋ ከርሞ በለስ ሲቀና በአሜሪካኖች ድጋፍ ሥልጣን ያዘና ለማረሳሳት ይሞክራል። ለማንኛውም፣ ለነጻነት ታገለ እንኳ ቢባል አሁን ይከፈለኝ፣ ብዘርፍ በወንጀል ብሰማራ መብቴ ነው ማለት ምን ትርጉም አለው?
  አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቂም በቀል ትተው፣ ጦር መማዘዝ ትተው፣ ለእኩልነት መታገል አለባቸው። እነ ለማ መገርሳ በወከላቸው ህዝብ ፊት የክልላቸውን ጥቅም ማስከበር መብታቸው ነው። በጠራራ ፀሐይ ህወሓት ቡናውን ወርቁን ከሰሉን የጋማ ከብቱን ጫቱን ዐረብ አገር የሚላኩ እህቶቻችንን፣ ለጉዲፈቻ ህጻናትን፣ ምኑን ሲያጋግዙ ዝም ተብለው ከርመዋል። ከንግዲህ መቆም አለበት።
  በአዲስ አበባ እና አካባቢው በልማት ስም ሕዝብ አፈናቅለው ለህወሓት መሪዎች (እንደ ቴዎድሮስ፣ ተስፋሚካኤል፣ ወዘተ) የተላለፈው መሬት መመለስ አለበት። አላሙዲ በጠራራ ፀሐይ ህወሓትን እየቀለበ የዘረፈው መቆም አለበት። አላሙዲን ባለበት ክልል ያለው መስተዳድር ውሎችን እንደ ገና መርምሮ ለአካባቢው ሕዝብ በሚጠቅም መንገድ ማቃናት አለበት። “ፌዴራል” ነው በሚል ሰበብ የሚካሄደው ሌብነት መቆም አለበት።
  ኦሮምያ ከአማራ ጋር ያለውን ቁርኝት የበለጠ ማጠናከር አለበት። ወደ ኋላ መመለስ የማንችለውን የድሮ ወሬና ቂም ትተን የዛሬውንና የነገን ትግል ማሸነፍ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። የኦሮምያ መሪዎች እነ ሌንጮ ለታ ካለማስተዋላቸው የተነሳ የህወሓትና የሻቢያን ምክር ሰምተው አንድ ትውልድ ለድንቁርና ማግደዋል። አማርኛ ሆነ እንግሊዝኛ ቋንቋ መማር ለመግባቢያና በአካባቢው ሥራና ፖለቲካ ለማሳተፍ ቁልፍ ሆኖ ሳለ፣ አማርኛ የጨቋኝ ቋንቋ ነው በሚል ወሬ ትውልዱን አራቁተዋል። ሌንጮ ራሱ በኦሮምኛ እንጂ በአማርኛ አልናገርም ያለበትን የጥጋብ ዘመን አስታውሳለሁ። የአማርኛ ቋንቋ እውቀቱ ከአማራ ያላነሰ ሆኖ ሳለ። ትግሉ በሁሉም መስክ በእኩልነት ዙርያ መሆን አለበት። ለዚህ የሚያስፈልገው መስዋእት የሚከፍሉ፣ ለጥቅማቸው የማያጎበድዱ መሪዎች ነው። ከዚህ ቀደም ያልታየው የሕዝቡ ከዳር ዳር መነሳት ነው። ህወሓት ሳያስበው የራሱን ጉድጓድ ቆፍሯል። ሕዝብ ከተንቀሳቀሰ የጦር መሳሪያ ብዛት አይገድበውም። ይኸ በታሪክ የተመሠከረ ነው። ህወሓት በፍርሃት መግዛት ሞከረ፣ አሁን ግን ተጋልጧል። በኦሮምያ ደም አፈሰሰ፣ በአማራ ደም አፈሰሰ፣ በወሎ ደም አፈሰሰ። የፈሰሰው ደም ሕዝቡን አስተሳሰረ። አሁን መመለስ አይቻልም። አርባ ጄኔራሎችን ሲሾም ህዝቡ አንተ ሞላጫ አጭበርባሪ ማንን ታጭበረብራለህ? አለው። ለማ መገርሳ እንዳለው፣ 6 ሚሊዮን ቄሮ ምን ልታደርግ ትችላለህ? የትግራይ ህዝብ ቢቆጠር 4 ተኩል ሚሊዮን ነው! አማራ ቴዲ አፍሮን ጋበዘ። የቴዎድሮስን ሐውልት አስመረቀ። ሕዝብ መመለስ አይቻልም። ኢሳት ሆነ አገር ወዳድ ድርጅቶች ከላይ የዘረዘርኩትንና ሌላም ማስረጃ በአጣዳፊ መሰብሰብ መጀመር አለበት። ለታሪክና ጊዜው ሲፈቅድ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው። ኢኮኖሚክስ ችሎታ ያላቸው በዚያ መስክ ይሰማሩ። ፖለቲካ፣ ፋይናንስ፣ ትምህርት፣ ወዘተ ሁሉም በየፊናው ተደራጅቶና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ አለበት።

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡