የፌዴራል ስርዓቱ ችግር በፖሊሲ ለውጥ አይቀረፍም!

በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በኢህአዴግና በጥቂት ግለሰቦች ተጽህኖ ስር የወደቀውን የፌዴራል ስርአት ተቋማዊ ማህቀፍ ለመስጠት ያስችላል ያለውንና “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ  ዴሞክራሲያዊ  ሪፐብሊክ  የመንግሥታት  ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ”  በሚል ርዕስ የቀረበለትን ረቂቅ የፖሊስ ማዕቀፍ እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል፡፡  የፖሊሲ ማዕቀፉ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት እንዲሁም በክልል መንግሥታት መካከል የሚደረግ የመንግሥታት ግንኙነት፣ በሕግና በተቋማዊ ሥርዓት እንዲመራ ለማድረግ የታለመ  መሆኑን ረቂቅ ፖሊሲው ያተታል፡፡


የኢህአዴግ መዋቅር፡ የፌዴራል ስርአቱ ተግዳሮት

የፌዴራል ስርአት በዋነኝነት ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው በማስተዳደር በሚመለከታቸው በተለያዩ ጉዳዮች ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል ስርአት እንደሆነ ምሁራን ይስማሙበታል፡፡ በዚህ መሰረት ውጤታማ የፌዴራል ስርአት ውሳኔዎች ከላይ እንደወረዱ የሚመጡበት ብቻ ሳይሆን ከታች ከህብረተሰቡ ወደላይ የሚሄዱበት ሂደትና ስርአት ሊኖረው ይገባል፡፡ የኢትዮጲያ የፌዴራል ስርአት ከተጀመረበት እለት አንስቶ በኢህአዴግ መዋቅራዊና ርዕዮተ አለም  ባህርይ የተነሳ ለዚህ አልታደለም፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲናEthiopia competing ethnic nationalism and the quest for democracy’’ በሚለው ጥናታዊ ስራቸው በኢህአዴግ መዋቅርና ባህሪይ የተነሳ የኢትዮጲያ የፌዴራል ስርአት እንደታሰበው እንዳይሰራ ሁለት ተግዳሮቶች እንዳሉበት ይጠቁማሉ፡፡

የመጀመሪያው ተግዳሮት ኢህአዴግ የሚከተለው የዲሞክራሲያዊ መዕከላዊነት (democratic centralism) በመባል የሚታወቀውና ከማርክሲስት-ሌኒኒስት ርዕዮተ አለም የተወሰደ ጽንሰ አሳብ ነው፡፡ በዚህ ጽንሰ አሳብ መሰረት ማንኛውም ውሳኔ የሚተላለፈው በማህከላዊ ኮሚቴ ሲሆን ከፌዴራሊዝም ጽንሰ አሳብ በሚቃረን መልኩ ውሳኔዎች ከላይ ነው የሚመጡት፡፡ ከታች ያለው የአስተዳደር መዋቅር ከላይ የመጣለትን ያለ ምንም ጥያቄ ተቀብሎ የማስፈጸም ግዴታ ስላለበት አካባቢያዊ ችግሮችን የሚፈታበት መንገድ የተገደበና ከላይ ያለውን አስተዳደራዊ መዋቅር ፈቃድ የሚጠይቅ ነው፡፡

ሌላኛው ፌዴራል ስርአቱ ተግዳሮት ተብሎ በዶ/ር መራራ የተቀመጠው በኢህአዴግ ውስጥ በየጊዜው የሚደረገው “ግምገማ” ነው፡፡ የተለያዩ ውሳኔዎች ከላይ ስለሚመጡና ማንኛውም የመንግስት አላፊም ሆነ ሰራተኛ የሚለካውም ሆነ ስራው የሚመዘነው ተቆጥሮ በተሰጠው መሰረት በመሆኑ  ከላይ የመጣውን ስራ እና ትህዛዝ የመተግበር አላፊነትና ግዴታ አለበት፡፡ ይህንን ባያደርግ “ግምገማ” በየጊዜው ስለሚኖርና በዚህም ተጠያቂ ስለሚደረግ ግምገማውን በመፍራት ከላይ የመጡትን አሳቦች ይፈጽማል፡፡ ይህም የፌዴራል ጽንሰ አሳብን ይጋፋል ይላሉ፡፡ እነዚህ ተግዳሮቶች የሚመነጩት ከኢህአዴግ ባህሪይና ካደገበት ርዕዮተ አለም የመነጩ ናቸው ይላሉ ዶ/ር መረራ፡፡

ከፖሊስ በፊት…

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የተነሳ ምንም አይነት ፖሊሲ ቢወጣና ምንም ቢደረግ የኢህአዴግ ባህርይ ካልተቀየረ የፌዴራል ስርአቱ እንደታሰበው በፖሊሲ ብቻ ሊሰራ አይችልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ፖሊስ ምንም እንኳን የፌዴራል ስርአቱን ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ ቢኖረውም ውጤታማ ሊያደርጉት የሚችሉ የተለያዩ ስራዎች መሰራት አለባቸው፡፡

በሀገራችን የሚታየው የፖለቲካ ፓርቲዎች ደካማነት፣ የሚዲያና የሲቪል ማህበራት አለመጠናከር፣ የዲሞክራሲ ማህበራ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር መውደቅና የሀገሪቱ ልሂቃን ዝምታና ከፖለቲካ መድረክ መገለል በአጠቃለይ የፌዴራል ስርአቱ ጠንካራ ተቋማት አለመፍጠሩ (weak institutions and structures) ትልቅ ተግደሮት ነው፡፡ እነዚህን ተቋማት ማጠናከርና ነጻ ማድረግ ካልተቻለ የፌዴራል ስርአቱ በተገቢው መልኩ ሊሰራ አይችልም፡፡

የፌዴራል ስርአትን በሚከተሉ አገራት የተለያዩ ልዩነቶችና ፍላጎቶች ስለሚኖሩ እነዚህን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ አስተሳሰቦች መኖራቸው አይቀርም፡፡ የተለያዩና የማይጣጣም የፖለቲካ ፍላጎቶችን (polarized political processes) ለማስተናገድ የሚያስችል ስርአትም እስካልተፈጠረ ድረስ ጠንካራ የፌዴራል ስርአት መገንባት አዳጋች ነው፡፡

እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ውስጣዊ ልዩነቶች (Sharp internal social divisions) ባለበት ሀገር ለዚህ ልዩ ትኩረት ተሰቶ ካልተሰራ ውጤታማ መሆን ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ልዩነቶች በተገቢው መልኩ መያዝ ካልተቻለ በህንድና ፓኪስታን፣ በናይጄሪያ፣ ይጎዝላቪያና ሮዴዢያ እንደታየው ወደ አላስፈላጊ ግጭት ሊያመራ ይችላል፡፡

በክልሎችና በህዝቦች መካከል ያለው የኢኮኖሚ እድገትና ተጠቃሚነት የተጣጣመ ካልሆነ ደግሞ ይበልጡኑ ስጋቱን ሊያባብስ ይችላል፡፡ ከ80 በላይ ብሔሮች ያሉባትና ከ70 በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገራችን የአብዛኛዎቹ ግጭቶቹ መንስኤዎች ከማንነትና ከብሔር ጋር የተያያዙ መሆናቸው የፌዴራል ስርአቱ ከፖሊሲ በተጨማሪ  ከዚህ ጋር የተያያዘ ጉዳዮች ላይ አጥብቆ መስራ እንዳሉበት ያሳያል፡፡

One thought on “የፌዴራል ስርዓቱ ችግር በፖሊሲ ለውጥ አይቀረፍም!

 1. በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የገዢውን ፓርቲ ስራአት በመቃወም በተለያዩ ጊዜያት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን ተቃውሞዎች ይቀሰቀሱ ነበር ።
  ሆኖም ግን እነዚህ ተቃውሞዎች በጭራሽ ህብረትና አንድነት ካለመኖሩም በላይ እንዲሁ ከመቃወም ያለፈ አላማና ስልት አልነበራቸውም ይህ ባለመሆኑ ምክንያት ለገዢው ፓርቲ እጅግ ጠቃሚና ምቹ አጋጣሚዎች ፈጥረው አልፈዋል ።
  ገዢው የወያኔ መንግስትም ያለማንም ጠያቂና ገላጋይ እጅግ አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ መልኩ በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ አስከፊ የሆነ በደልን ተፈፅሟል ።
  #ብዙዎች #ሞተዋል_ታስረዋል_አካላቸው_ጎድሎዋል_በከፍተኛ_ደረጃ_ተሰቃይተዋል_ሰብአዊ_መብታቸው_ተገፎ_ከትውልድ_ሀገራቸው #ተሰደዋል_ተባረዋልም_ንብረታቸውም_በግፍ_ተወርሷል_ተዘርፈዋልም !!!
  ኧረ ምኑ ቅጡ ተወርቶ ያልቅና ይህቺ አህገር ምን ያላየችው አለና እነዚህን ጥፋቶችን ለመፈፀም የተለያዩ አዋጆች እና ህጎች እየወጡ ይፀድቁ ነበር ህጎቹም አፋኝና ከልካይ እንደ መሆናቸው መጠን ለወያኔ መንግስት ጊዝያዊ መፍትሔ ሰተው ነበር ።
  ሆኖም ግን ዘልቀው ሊጓዙ አልቻሉም በተለይም ከ 2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በህዝቡ ላይ የተሰሩ የተለያዩ ወደ አንድነት የሚያመጡ ስራዎች በሚያስገርም መልኩ ከፍተኛ የሆነ ስራ ተሰርቷል ይህንን ምግባር መቼም ቢሆን ታሪክ አይዘነጋውም ለትውልድም ሲዘከር ይኖራል በመጀመርያ #የኦሮሞን_ህዝብ በሸዋ በወለጋ በባሌ በሀረርጌ በአርሲ በቦረና በጉጂ በብዙ ከተሞቻችን ብቻ ዘርዝሬ አልጨብቻረሰውም የነበረውን በአንድነት የመንቀሳቀስና የመደጋገፍ #የኦሮሞ ህዝብ በጠንካራና በአንድነት እንዲነሳና እንዲዋደድ የተለያዩ የትግል ስልትና አመራርን በመስጠትና እንደ #ቄሮ ያለን ጠንካራ ታጋይና የትግል ስምና ስልት በመፍጠር የወያኔ መንግስት ላይ ከፍተኛ የሆነ የማንኮታኮት የማናጋት ስራዎች እንዲሰሩ ታላቅ አስተዋፆ ያበረከቱ ብዙ የኦሮሞ ልጆች እንዳሉ እየገለፅኩ ትልቁን ሚና ለተጫወተው ምርጡ
  #የኢትዮጵያ_ልጅ #ለጃዋር_መሀመድ_Jawar_Mohammed ያለኝን ታላቅ ፍቅርና አክብሮት ሳልገልፅ አላልፍም ።
  በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አንድነት በመፍጠርና እንደ #ከግንቦት_7እና_ፋኖ ያለ ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው በማለት የመተባበርና የአብሮነት ፍቅር እንዲፈጠር የማይዘነጋ ታላቅ የሆነ ታሪክ ሰርቷል ታሪክ ብቻም አይደለም ለዘመናት በከፍፋለህ ግዛ ስረአት ውስጥ የወደቁ የተጋደሉ የተጣሉ የተቀያየሙ ህዝቦችን አስታርቀዋልም ከዚህም ታላቅ ምግባር ጀርባ #የፕሮፌሰር_ዶ/ር #ብርሀኑ_ነጋ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ።
  ይህ ሁሉ አንድነት ባይኖርና አሁን በጥቂቱም እንደምናየው የተስፋ ጭላንጭል ብርሀን ባላየን ነበር ።
  #ባጠቃላይ_ይህ_ሁሉ_ሲሆን
  * ታላላቅ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራርና አባትላ
  * የኢንተርኔት አምደኞች * ጋዜጤኞች ሙዚቀኞች
  * የታላላቅ የትምህርት ተቋማት መምህሮችና የኢትዮጵያ ተማሪዎች በጠቅላላ
  *አንዳንድ የክልል ፖሊስ ወታደሮችና
  *ጥቂት የመንግስት ሰራተኞች ብቻ ባጠቃላይ የብዙዎች ተሳታፊነትን ያቀፈ ነበር ።
  በዚህ ትግልና ንቅናቄ #በወያኔ #መከላከያ_ሰራዊት_ተገድለው #ህይወታቸው_ላለፉ_አካላውቸን_ላጡ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ መፅናናታችሁ ይብዛ !!! ለሁላችንም የተሻለች የኢትዮጵያን የምናይበት ጊዜና ዘመን ይምጣልን እላለሁ ቸር ሰንብቱ።

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡