መ/አ አይዳ አሌሮ ማን ናት? (በማስረጃዎች የተደገፈ ግለ-ታሪክ)

መ/አለቃ አይዳ አሌሮ ማን ናት?

መ/አለቃ አይዳ አሌሮ ሐሙስ ግንቦት 09/2010 ዓ.ም ወታደራዊ ፍርድ ቤት ትቀርባለች፡፡ ከዚያ በፊት ግን ስለ ስራዋ፣ ስለ ተከሰሰችበት ምክንያት፣ እንዲሁም ስለ ተከሰሰችበት ምክንያት በማስረጃ አስደግፈን ግለ-ታሪኳን እንደሚከተለው አቅርበንዋል፡፡

 • ስም፦ አይዳ አሌሮ
 • የትውልድ ቦታ፡- አ.አ ክ/ከ ቂርቆስ ወረዳ 20/21
 • የቤት ቁጥር 121 አካባቢው ፍላሚንጎ/ደንበል ጀርባ
 • የአንደኛ ደረጃ ትምህርት፦ ነፃነት ብርሃን ት/ቤት 35 ሜዳ ወደ መስቀል ፍላወር
 • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፡- ከ9-10 ቦሌ መድኃኔዓለም ት/ቤት
 • የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፡- 10+1 ምስራቅ አጠቃላይ 22 አካባቢ የትምህርቱ አይነት ድራፍቲንግ
 • ወደ መከላከያ ሠራዊት የተቀላቀልኩት በ1997 ዓ.ም ሲሆን የሥልጠና ቦታው ብር ሸለቆ የምልምል ወታደሮች ማሠልጠኛ፣ የስልጠናው ግዜ 6 ወራት፡፡

 • ከሥልጠናው በኃላ የሥራ ምደባ፡- አጋዚ ቶጋ ዋና መምሪያ የሚገኝበት ቦታ ሐዋሳ የቆይታ ጊዜ ከ3-4 ወራት አካባቢ፡፡
 • የኮማንዶ ስልጠና፦ በብላቴ የልዩ ኃይሎች ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ፓራሹት ስልጠና፡፡
 • የፓራሹት ዝላይ ብዛት፦ 27 ጊዜ

 • የውትድርና ማዕረግ፦ ም/መ/አ ወደ ሁርሶ በመሄድ በ2009 ዓ.ም ስቀበልም ከ1800 ሰልጣኞች ውስጥ በአንደኝነት አጠናቅቄያለሁ፡፡

  • የኃላፊነት ደረጃ፦ አ/ወለይ/ማ/ት/ቤት የፓራሹት ጠቅላይ ዲፓርትመንት ኃላፊ

  የክሱ ሁኔታ
  ሁመራ ላይ ከሽብር ቡድን ጋር በመገናኘት
  ውስጥ ለውስጥ ሠራዊቱን በማነሳሳትና በማስከዳት ወደ ሽብር ቡድን በመግባት ስልጠናዎችን በመስጠት፣ በተቋሙ ውስጥ የነበሩትን መረጃዎች ለኦነግ እንዲሁም ለአርበኞች ግንቦት 7 በማስተላለፍ፣ ከቀድሞ የደርግ ሠራዊት ጋር በክፍሉ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች በመለዋወጥ፣ ኮብልለው ከሄዱ የአየር ኃይል አባላቶች ጋር እንደሚኮበልሉ እያወቀች መረጃ በመደበቅ፣ በ2006 ዓ.ም ወደ ሱማሌ የሰላም ማስከበር ግዳጅን አልቀበልም ብላለች የሚል ነው፡፡

  እነዚህ ክሶች ምንም ማስረጃ የሌላቸው በመሆኑ ክሱን ወታደራዊ ችሎት ቤላ ወደሚባለው አካባቢ በኩብለላ በማድረግ ቀይረውታል፡፡ ሌላው ተቀጥቼ (ተፀፅቻለሁ) ብዬ የምል ከሆነ በ3 ወር የዲስፒሊን ቅጣት ወደ ቦታ ለመመለስ፣ ይህ ካልሆነ ግን ከ10 – 15 አመት እንደምቀጣ አስጠንቅቀውኛል፡፡

  2 thoughts on “መ/አ አይዳ አሌሮ ማን ናት? (በማስረጃዎች የተደገፈ ግለ-ታሪክ)

  1. ። አይዳ የማትኮራ ተጫዋች ስላምተኛ ናት። ሌሎች የርሷ ጓደኞች ተቋሙን ጥለው ቢወጡ የርሷ አይነት ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ለማስተማር በሚል ብዙ ስቃይ እንዳሳለፈች እገምታለሁ ። ወደ ስራም ብትመለስ ክብር አይሰጧትም የበለጠ በሞረሏ ላይ ይጫወቱባታል። ቢበዛ ከ3—5 አመት ቢፈርዱባት ነው ። ማስፈራርያው ላይ አታቶኩሩ ህግ ነው የሚዳኘው በተቻለ መጠን አዋ ከድቻለሁ ብላ የእስር ማቅለያው ላይ ትኩረት አድርጋችሑ ስሩ የተወሰነ ጊዜ ታስራ ነፃነቷን ብታገኝ ይበልጣል ። አይዳ መጠንከር አለብሽ

   Like

  አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡