የአማራ ብሄርተኝነት፣ ኦሮማራ እና ኢትዮጲያዊነት!

By Roobaa Qaasim
የዛሬ አምስት አመት ኦሮሞና አማራ አንድ ናቸው፣ አንድም መሆን አለባቸው ብዬ ስጮህ ነበር… አሁንም ተመሳሳይ አቋም አለኝ። ያኔም አማራ ሆኜ ሳይሆን ያለውን ችግር ስለተረዳው ነው። ዛሬም እምነቴ ያው ነው። አማራው ትላንትም ተበድሏል፣ ዛሬ ደግሞ የባሰ በደል ውስጥ ነው ያለው።

ከአማራ ልጆች (አክትቭስቶች) ጋር ያለኝ ልዩነት አማራን (የአማራን ብሄርተኝነት) ከኦሮሞ ብሄርተኝነት ጋር ተቃራኒ አድርጎ ለመሳል በመሞከራቸው ብቻ ነው። ይህ አደገኛ አካሄድ ነው። እሱ ብቻ አይደለም። በፍጽም ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሚያስመስል አካሄድም አላቸው። በሌላ አነጋገር ጽንፍ የያዙ ይመስላል፡፡በበኩሌ “ለአማራ በደል መጮህ/መቆምና ጽንፈኛ መሆን የተለያዩ ናቸው” የሚል እምነት አለኝ። ለኦሮሞም ቢሆን እንደዚያው ነው።

ለአማራ ብሄርተኝነት አቀንቃኞች ወይም አክትቭስቶች ያለኝ ምክር “ልክ እንደ ትላንቱ አሁንም ከኦሮሞ ጋር ቁሙ” የሚል ነው። አሁንም እንደ ትላንቱ ኢትዮጵያን አትልቀቁ። አማራነትና ኢትዮጵያዊነት በምንም ታኣምር አይጻረሩም። ኦሮሞም እንደዚያው ነው። ኦሮሞነትና ኢትዮጵያዊነት ተቃራኒ አይደሉም። ስለዚህ የአማራና ኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ጋር በመሆን (ሌሎቹንም በማስተባበር) ልክ እንደ ትላንቱ እንደ ብሄር እና እንደ ሀገር የተቃጣብንን ብሄራዊ ውርድትን እንታገል። ችግሩን እንወጣው፤ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወደ መቃብር እንክተተው። ይህንን ደግሞ በተግባር ጀምረንዋል።

የተጀመረውን እናስቀጥል፤ አንድነታችንን እናጠናክር። የለማ ቡድንን እና ገዱን እንርዳቸው፡፡ ለለውጥ እንቁም ወይም ለውጡን እናግዝ! የወያኔ ፋሽስት/አፓርታይድ ስርኣት ማፈራረስ በጋራ እንደጀመርነው ሁሉ ተባብረን እንጨርስው።
በምንም ታኣምር ከኦሮሞ ወንድሞቻችሁ ጋር አትጋጩ፡፡

ዛሬም የአማራው በደል የኔም በደል ነው! አመሰግናለሁ!


ምንጭ፦ የሮባ ቃሲም ፌስቡክ ገፅ

2 thoughts on “የአማራ ብሄርተኝነት፣ ኦሮማራ እና ኢትዮጲያዊነት!

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡