እነ መላኩ ፈንታን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት፣ 17 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጠየቀ።

አቶ መላኩ ፈንታ እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ

ከሁለቱ ግለሰቦች በተጨማሪም አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ አቶ ጌቱ ገለቴ፣ አቶ ገብረስላሴ ገብረ፣ አቶ ስማቸው ከበደ፣ ኮሎኔል ሀይማኖት ተስፋዬ፣ አቶ ገምሹ በየነ፣ አቶ ፍፁም ገብረመድህን፣ ኬኬ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ጌታስ ኩባንያ፣ ኮሜት ትሬዲንግ ሀውስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ነፃ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ክሳቸው እንዲቋረጥ ተጠይቋል።

በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሙስና ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ዓለማየሁ ጉጆ፣ አቶ ዋስይሁን አባተ፣ አቶ አክሎክ ደምሴ፣ አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል፣ አቶ ዘርፉ ተሰማ፣ አቶ መስፍን ወርቅነህ፣ ወይዘሮ ሰኸን ጎበና፣ አቶ ጌታቸው ነገሪ፣ አቶ ነጋ መንግስቱ፣ አቶ ሙሳ መሀመድ፣ አቶ ሲራጅ አብዱላሂ፣ ኮሎኔል መላኩ ደግፌ፣ ትርሲት ከበደ፣ ገዛኸኝ ኢጀራ፣ ቤዛዓለም አክሊሉ፣ ወንድሙ መንግስቱ፣ አቶ ቢልልኝ ጣሰው እና ማህደር ገብረሃናን ክስ እንዲነሳ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ ፍርድ ቤቱ በእነ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ በተዘረዘሩት ተከሳሾቹ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ቢሰጥም ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመር መዝገቡን ማቋረጥ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ስላመነ ጉዳያቸው እንዲቋረጥ ጠይቋል።

በተጨማሪም ድሪብሳ ዳምጤ፣ አንበዶ ጎንፋ፣ ዓለሙ አንበሳ፣ ዋቆ መርጋ፣ ሞሲሳ ዳግም፣ ሌሊሳ መርጋ፣ ሙሉ በለጠ፣ ፍቃዱ ቶሎሳ፣ ፀጋዬ ዓለሙ፣ በዳዳ ድሪብሳ፣ ታሪኩ በዳሳ፣ ረመዳን መሀመድ፣ በዳዳ አያና፣ ግርማ ወርቅነህ፣ ወዬሳ በቀለ፣ አህመድ ኢብራሂም፣ አብዮት አበበ፣ መሀዲ አልዬ፣ እስማኤል ዑመር፣ አህመድ አደም እና አብዱልሰመድ አህመድን ጨምሮ 137 ተከሳሾች ክስ እንዲነሳም ነው የጠየቀው ።

አቃቤ ህግ የግለሰቦቹ ክስ እንዳቋረጥ እና እንዲነሳ የጠየበትን ደብዳቤ ዛሬ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያስገባ ሲሆን፥ ፈርድ ቤቱም ጥያቄውን እንደተቀበለ ግለሰቦቹ ከማረሚያ እንደሚለቀቁ ተመልክቷል።

በታሪክ አዱኛ


ምንጭ፦ FanaBC